የለውጥ ሃይሎች አባል የሆነው ስንታየው ቸኮል በደህንነቶች ታፈነ::

Minilik Salsawi የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው ስንታየሁ ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዶዋል።
ስንታየሁ ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ ትግል እራሱን ሰጥቶ ይታገል የነበረ ጠንካራና ለትግሉም በምንም የማይደለል ታማኝ ወጣት ታጋይ ነው።
