ሀገ ወጡ ነጋዴ!
አንድ የንብ ሰዕል ያለበት ቲሸርት የለበሰ ህገ ወጥ ነጋዴ መንገድ ላይ ቆሞ ሲለፈልፍ አየሁት!
”ፓርቲ ፓርቲ… ሁለት የቀረች ፓርቲ….”
ይላል።
ነገሩ እንግዳ ቢሆንብኝ፤ ፓስቲ ፓስቲ ማለቱ ነው ይሆን… ስል እያሰብኩ ጠጋ ብዬ ሰማሁት።
”ፓርቲ ፓርቲ ሁለት የቀረች ታላቅ ቅናሽ….”
ቁልጭ ብሎ ተሰማኝ ፓርቲ ፓርቲ ነው የሚለው።
የኔ ወንድም የምን ፓርቲ ነው የምትሸጠው… ብዬ ብጠይቀው ደፍሬ እንደማልገዛው ገምቶ ይሁን፤ ወይ ደግሞ መናገር እንጂ መስማት የማይችል ሆኖ ይሁን እንጃ መልስ ሳይሰጠኝ መለፍለፉን ቀጠለ…
”ፓርቲ ፓርቲ ታላቅ ቅናሽ…. አላየንም አልሰማንም እንዳትሉ! ታይቶ በማይታወቅ ዋጋ… ፓርቲ ፓርቲ… ሁለት የቀረች…”
ግራ ግብቶኝ ሳለ፤ አንድ አየለ ጫሚሶ በአካባቢው አለፍ ሲሉ፤ ነጋዴው በፈገግታ አያቸው… አይቶም ዝም አላላቸውም፤
”ደንበኝ አማን ነው…!” አላቸው፤ አየለ ጫሚሶውም ምንም መልስ ሳይሰጡት ጠጋ አሉት እና፤ አንድ መዝገብ ከነጋዴው ስር አንስተው በጉምጀት እያዩዋት፤
”ይቺ ፓርቲ አሪፍ ነበረች”
ሲሉ ሰማኋቸው፤ የያዙትን መዝገብ ልብ ብዬ ሳየው ”አንድነት” ይላል። ሀገ ወጡ ነጋዴ የማይሰማ የመሰልኝ ለካስ እየመረጠ ሰለሚሰማ ነው እና፤ እጃቸውን አፈፍ አድርጎ ይዞ፤
”እርሷ ተይዛለች ሰውዬው ካልመጡ ይወስዷታል!” አላቸው።
ይሄን ጊዜ በርካታ ወጣቶች፣ ትልልቅ ሰዎች፣ ሴቶች እና ልጆች ሳይቀሩ፤
”በህግ አምላክ… ሰርቆ ነው የሚሸጠው…. በህግ አምላክ የኛ ንብረት ነው በህግ አምላክ ሀገ ወጥ ንግድ ነው….በህግ አምላክ”
እያሉ ከነጋዴው ጋር ሲተናነቁ ተመለከትኩ!