ኢሳትና አንድነት
ኢሳት የሚድያ ተቋም በበርካታ ሽህ ማይሎች ርቀት ላይ የሚገኝ ላገር ያስባል ተብሎ የተቋቋመ ድርጅት ነዉ፡፡እንደሚለዉ የኢትዮጵያዉያን አይንና ጀሮ ይሆናል ብለንም አስበን ነበር፡፡የኢድቶርያል ቦርዱን ፖሊሲ ብናዉቀዉ ደስ ባለን፡፡መስራቾች ብዙ ለፍተዉና ሩቅ አልመዉ እንዳቆሙት ይታመናል፡፡አንድነትን በፖሊሲ ደረጃ እየታገሉት ከሆነ ያሳዝናል፡፡የሁለትና ሶስት ጋዜጠኞች የግል ፍላጎትና ጨዋታ ከሆነም እናያለን፡፡
እንዳለመታደል የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ባለብዙ ሚድያ፤ባለ ሙሉ ጦርና(ፌደራል ፖሊስ) ያገር ሃብት ይዞ ለሚያፍነን ፀረ ዲሞክራሲና አንደነት የሆነዉን ስረኣት እየታገልን ለዚህ ድርጊት የምንሸበር አንሆንም፡፡እነዚህ ጋዜጠኞች ግን የአንድነትን አወንታዊ የሰላማዊ ትግሉን እንቅስቃሴ፤የተመዘገበዉን ዉጤት ሳይሆን የእስርና እንግልት እንደሚያጎሉት እናዉቃለን፡፡ እኛ የጣልነዉን ወይ የወደቀብንን በማንሳት የኢቲቪን ስራ ሲደግሙብንም እንታዘባለን፡፡ይህንንም ከዚህ በፊት በሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት ግዜ በግብረሃይሉ ተገምግሞኣል፡፡
ብሶታችንን ብቻ ሳይሆን ያሉንን አማራጮች፤ስልተና እስትራተጂክ ግባችንን እንድናብራራ ቅርብ ያለዉ ሲዘጋብን እነሱዉ ቢከፍቱልን መላካም ነበር፡፡የሚፈልጉን ለብሶት ከሆነ ህዝቡ በቅርብ ስለሚያዉቀዉ ብዙም አያምሩንም፡፡ህዝቡ እንዲደራጅና ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ጉልበት እንዲኖረዉ ቢያስተምሩ በጎ ነበር፤እንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና የፓርላማ አባል ከሌላ ፓርቲ የፓርላማ አባልና የግዜዉ ባለስልጣን ተጨባበጠ ብሎ ክስ ግን ያስገምታል፡፡አንድነት የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶን አምጥቶ መሪ፤እነ ሃብታሙ አያሌዉን ከፍተኛ አመራር… ያደረገበትን አገራዊ ፋይዳ የዘነጉት ይመስለኛል፡፡ዛሬም የአንድነት በር ወንጀለኛ ላልሆነ የኢህአዴግ አባልና ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሩ ክፍት ነዉ፤ለዉይይትም ለትግልም፡፡
ሚድያ ናቸዉና ከሰራን ይዘግባሉ፡፡አንድነቶች በያለንበት ወደ ስራ!!! ሰላማዊ ለዉጥ እንዲመጣ የበኩላችሁን ገንቢ አስተዋፅኦ ለምታደርጉ የየትኛዉም ሚዲያ አይነት አካለት ግን በግሌ ክብር እሰጣለሁ፡፡ኢሳትና አንድነት ባላንጣም፤ወዳጆችም ሊሆኑ አይችሉም፡፡
ለለዉጥ እንደራጅ!!