በዋሽግተን ዲሲ የሚገኘዉ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን የ አቋም መግለጫ አወጣ

Image

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰዉን በድልና ጭቆናን በመቃወምና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችአስመልክቶ በዋሽግተን ዲሲ የሚገኘዉ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን የ አቋም መግለጫ አወጣ
ባለስድስት ነጥብ የሆነዉ የ አቋም መግለጫ የ ኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮች ያጠቃለለ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚያደርሰዉን በደልና ጭቆና ለመታደግ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን አገራዊ ሐላፊነቱን ለመወጣት የሚጠበቅበትን ሁሉ እደሚያደርግ የ አመራር አካላቱ ለ ቢቢኤን ገልጸዋል። የአቋም መግለጫዉም እንደሚከተለዉ ይነበባል፦

• ሆን ተብሎ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ መንግስት ሲፈፅም የቆየዉን ኢሰብአዊ ድርጊት ባዲስና በከፋ መልኩ የጀመረዉን እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

• ሙስሊም እህቶቻችንን የእምነት ነፃነት በመንፈግ ባአዲስ አበባ ዩኒፈርሲቲና በሌሎች የትምህርት እንዲሁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ሂጃባቸዉን እንዲያወልቁ የማስገደዱ ጉዳይ ሙስሊም ሴቶችን ከእምነታቸዉና ከትምህር እንዲሁም ከእምነታቸዉና ሰርተዉ ከመኖር ምረጡ እየተባሉ የሚደረግባቸዉን ተፅእኖን አጥብቀን እናወግዛለን

• በግፍ ታስረዉ ባሉት የሙስሊም መሪዎች ቤተሰቦች ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ ገብታችሁ ወዳጆቻችሁንን መጠየቅም ሆነ ምግብ ማቅረብ አትችሉም ተብለዉ የሚደርስባቸዉን መጉላላት በጥብቅ የምናወግዝ መሆናችንንም እንገልፃለን

• እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካንድ ጠቅላይ ሚንስቴር በማይጠበቅ አፀያፊ አነጋገር ጨዋዉንና ታታሪ ሰራተኛዉን የስልጤን ብሄረ ሰብ መዝለፋቸዉን አጥብቀን እንቃወማለን

• በቪዎች የሚቆጠሩትን ካገርና ከወገን ተለይተዉ ቤተሰቦቻቸዉንና ዘመዶቻቸዉን ለመርዳት የሚደርስባቸዉን ያካልና የመንፈስ ተፅእኖን በመቇቇም ለሚያደርጉት መስዋእትነት መመስገንናና መደነቅ ሲገባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ባልተገራ አንደበታቸዉ እህቶቻችንን ገረዶች ብለዉ አንቇሸዉ መጥራታቸዉ እጅጉን አስከፍቶናል። የኢትዯዽያ ህዝብንም ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ እናሳስባለን።

• በተጨማሪም በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች ላይና እንዲሁም ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣዉ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን ኢሰብአዊ መንግስታዊ እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

“ፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን የኢትዯዽያ መንግስት ከቀን ወደቀን የህዝቡን ሰብአዊ መብት እየጨፈለቀ መቀጠሉን አጥብቀን እንደሚያወግዝና ሌላዉም የሰዉ መብት ያገባኛል የሚል ስብእና ያለዉ ሰዉ ያወግዝ ዘንድ ጥሪዉን ያቀርባል” በሚል የጥሪ መልክት የ አቋም መግለጫዉ ተቋጭቷል። የፈርስት ሒጅራህ የአመራር አካላት መጠነ ሰፊ የሆነዉን ጭቆናና በደል ለመታደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንደሚሰሩ በመግለጽ በቀጣይነትም የሚያከናዉኗቸዉ የተቃዉሞ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩ ለቢቢኤን ገልጸዋል።