“ፓርቲዎች መብታቸውን ለማስጠበቅ ተባብረው ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማካሄድ ግድ ይላቸዋል” – የአንድነት ፓርቲ የመብት ጥያቄ እና ምርጫ ቦርድ ተፋጠዋል::

በመግለጫ ነገር መወራወር የጀመሩት የተቃዋሚ ፓርቲእ አንድነት እና የወያኔው ምርጫ ቦርድ መላተም መጀመራቸውን ከዙሪያቸው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ በዚህም መሰረት የኢሕአዴግ ተቋም የሆነው የምርጫ ቦርድ አንድነት እና መኢአድን ከ2007 ምርጫ ውጪ ለማድረግ ዳር ዳር እያል ነው ሲሉ አንድ የአንድነት ከፍተኛ አመራር ጽፈዋል:: ከፍተኛ አመራሩ በጽሁፋቸው እንዳሉት የኢህአዴግ ጎፈሬ ከማበጠር ውጪ ምንም ፋይዳ የሌለው “የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ” አንድነትንና በመኢአድን በምርጫው እንዳይወዳደሩ ለማድረግ ላይና ታች እያለ ይገኛል ያሉት አመራሩ እነዚህ ፓርቲዎች ባለፈው ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም. ውህደት ለመፈፀም ተስማመተው የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፤ ውህደቱን የከለከለውና እንዲሰናከል ያደረገው ይሄው ምርጫ ቦርድ ተብዬው የመሸጦ ተቋም ነበር። በማለት በጽሁፋቸው አስፍረዋል::

አሁን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ግልፅ እየሆነ ያለው ነገር የዚህ ምርጫ ቦርድ ዋና ዓላማ ፓርቲዎች ተጠናክረው እንዳይወጡ መከላከልና የኢህአዴግ ወንበር መጠበቅ እንደሆነ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም።ያሉት አመራሩ አያይዘውም ከእንግዲህ ይለይልናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል::

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከአሁኑ እንዲጀምር እድል ተፈጥሯል ማለት ነው። አሁን ነው ወገብን ጠበቅ አድርጎ አመራር ለመስጠትና ለመታሰር ዝግጁ መሆን የሚያስፈልገው። እኛ የምንችለው ሁሉ አድርገናል ከዚህ በኋላ የፈለገው ቢሆን የሚፀፅተን ነገር አይኖርም።ሲሉ ህዝቡ ለህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲዘጋጅ እድሉን እንዲጠቀምበት መሪ በመሆን የሚፈለግባቸውን ድርሻ ለመወጣት ፓርቲያቸው መዘጋጀቱን አሳውቀዋል::

የአንድነት አመራሩ እንዳሉት ፓርቲዎቹ በምርጫው እንሳተፋለን ሲሉ፤ ምን አስበው ነው ተብሎ የለም አትሳተፉም የሚባል ከሆነ ይህን መብታቸውን ለማስጠበቅ ተባብረው ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማካሄድ ግድ ይላቸዋል ማለት ነው። መቼም ዘንድሮ በኢህአዴግ ቤት ማሰቢያው ጨርሶ እንደጠፋ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም፤ እዚያ ቤት ግን የተፈጠረው ነገር ምን ይሆን? ሲሉ ጽሁፋቸውን ድል የህዝብ መሆኑን በመግለጽ አጠቃለዋል::
Image