ይነበብ 40ኛው ዓመት የህወሐት ልደት በዓልና ሽርጉዱ ከኣስገደ ገ/ስላሴ መቐለ

Image

ህ.ወ.ሐ.ት 40ኛ ዓመት በዓሉ ለማክበር እያደርገው ያለው አከባበር ከመግለጼ በፊት የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ለምን የትጥቅ ትግል መረጡ የሚለውን ትንሽ ለአንባብያን መረጃ ሰጥቼ ልለፍ፡፡ ህ.ወ.ሐ.ት የመሰረቱ ሰዎችና የትግራይ ወጣቶች ነፍጥ አንስተው ደርግን በጦርነት አስወግደው የደርግን ስርዓት ለመለወጥ የተነሱበት ዋናው ምክንያት ደርግ ዘውዳዊውን ስርዓት አሰወግዶ በትረ-ሥልጣኑ የጨበጠው ራሱ ታግሎ ያመጣው ለውጥ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሙሁራኖች፣ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ አረሶ አደሮች፣ ወዝ አደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች ወ.ዘ.ተ በተደራጀና ባልተደራጀ መንገድ ያነሱት ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ዘወዳዊው ስርዓት ሊመልሰው ሰላልቻለ የበሰበሰው መዋቀሩ በመፍረክረኩ ደርግን ያን አጋጣሚ ተጠቅሞ ስልጣኑን ሊጨብጥ አስቻለዉ፡፡

እነዛ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ አንስተው ፤ዘውዳዊው ስርዓት ያፍረከረኩ ወገኖች ደርግ በግብታውነት በትረ ስልጣኑን በመያዙና እነዚ የህዝቦች ዲሞክራሳያዊ ጥያቄዎች ደርግ በሚድያና በዲኘሎማሲ በመደናገር የህዝባችን ጥያቄ በመቀልበስ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ የሆኑ አምባገነን አዋጆች በማወጅ ህዝባዊ ማዕበሉን በማፈን ሁሉም ዓይነት ጥያቄዎች ገና በጥዋቱ ማፈን ጀመረ፡፡

ደርግ የአምባገነንነቱና ፋሽስታውነቱም መግለጫ የዘውዳዊው ስርዓት ከ60 በላይ ሚንስትሮች ፡ ጀኔራሎች በመሰበሰብ በጥይት ደብድቦ ገደላቸው ፤ የህዝቦች ሰለማዊ ትግል ደርግ በዜጎች ደም ታጥቦ ትግሉን አኮላሸው፡፡ በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ህዝባዊ መንግሥት ሊመሰረት አልተቻለም፡፡ መድበለ-ፓርቲ ፡ ዩንር፣ሁሉም ዓይነት ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የሃይማኖት ነፃነት፣ ፍትህና የህግ የበላይነት ይከበር፡ የሚሉ ጥያቄዎች መልሳቸው ልክ አሁን የህ.ወ.ሐ.ት/ኢህአዴግ መንግሥት እያደርገው ያለው ዓይነት እምቢ ላለሰው፤ እሰረው ፡ ግረፈው፡ ግደለው፡ እንደሚለው ያለው ደርግም እምቢ ላለሰው ጥይት አጉርሰው ብሎ አወጀ የህዝቦች ጥያቄዎች አፈናቸው ፡፡
በዛን ግዜ የኢ/ያ ህዝቦች በተለይ በንቃተ ህሊና ትንሽ መጥቀው የነበሩ ሙሁራንና ሰራተኛች በደርግ ስርዓት ሰለማዊ ትግል ለማድረግ አይቻልም በማለት በረሃ ወጥተው የትጥቅ ትግል ለማከላሄድ ወሰኑ፡፡ አንዳ አንዶቹም ደርግ በትጥቅ ትግል ሳይሆን በከተማ ነውጥ ነው ማስወገድ የሚቻለው በማለት የነውጥ ስትራቴጂ መርጠው መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር፡፡ በሌላ በኩል ከደርጎን በመሆን በጎ በጎውን መንገድ እንዲከተል መንገድ በማሳየት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማድረግ ይቻላል አሉ፡፡ ይህ የዘመኑ ሙሁር የየራሱ የተለያየ ፍልስፍና በመያዝ በየፊናው በመዝመት በአንድነት ታግሎ ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ መንግሥት የመመስረት የህዝቡን ተስፋ አጨለመበት፡፡ በአንፃሩ የዚያን ጊዜ ሙሁራን በየፊናቸው ተደራጅተው በሃገራዊና ብሄራዊ ጥያቄ ሥር ብዙ ፀረ-ደርግ የፖለቲካ ኃይሎች ተመሰረቱ፡፡
ከነዚህ ውስጥ የትጥቅ ትግል ስትራቴጂ ከመረጡት ውስጥ አንዱ ህ.ወ.ሐ.ት ነበር፡፡ በህቡዕና በግልፅ ተደራጅቶ በየካቲት 11/06/1967ዓ.ም በ11 ሰዎች በረሃ ደደቢት ወጥቶ የጥቅ ትግል ጀመረ ፡፡ እኖሆ ህወሐት ዘንድሮ 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ለማክበር ሸርጉድ እያለ ይገኛል፡፡
ህ.ወ.ሐ.ት ዩዞዋቸው የተነሳ ዓላማዎች፡-
አባገነኑን ፋሽስታዊ ደርግን በማስወገድ ህዝባዊ መንግሥት መመስረት፡
የመድብለ-ፓርቲ ስርዓት እንዲኖርና በነፃ የመደራጀት፣ ነፃ የምርጫ ውድድር መኖር እንዳለበት፡፡
የብሄራዊ መብት የራስን ዕድል በራስ መወሰን ዕድል እንዲይኖር ፡፡ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ መሆኑ፡፡
ብሄራዊ ትግል እንደ የሰልት ትግል ተጠቅሞ መደባዊ ትግሉን እዳር በማድረስ ለኢትዮጵያ አንድነትና እኩልነት መታገል ፡፡
የገጠርና የከተማ መሬት የህዝብ መሆን እንዳለበት፡፡
በፖለቲካም ማርክሰሌኒናዊና ማአዘዲንጋዊ ስነ ሃሰሳብ መመሪያው እንደሆነ፡፡
የአብዮቱ ጠላተች፤ ፉሽስታዊ ደርግ፣ መስፍናዊ ስርዓት፣ ሃብታም ገበሬ ፡ ሃገራዊ ባለ ሃብት፣ ከፍተኛ ሙሁርና ኢንፔርያሊዝም እንደሆኑ ፡፡

ከላይ የተጠቀሰው የኃይል አሰላለፍ በፅሁፍ ተሰንዶ በማኒፈስቶ ደረጃ የተቀመጠ አልነበረም፡፡ እንዲሁ በሰመበለው ነበር የሚነገረው ፡፡ እላይ የተዘርዘረው አÌም የህ.ወ.ሐ.ት አÌም ሆኖ አልቀጠለም ፡፡

በ1968 ዓ.ም አጋማሽ አከባቢ ግን አንድ አስደንጋጭ አÌም ተያዘ፡ ይህ አÌም ታጋዮች ተዋይተውበት ወይም በድርጅቱ በጉባኤ ቀርቦ የፀደቀ አልነበረም፡፡አማራሩ አስቦበት አትለው በግብታውነት አትለው የመጣ አቋም ነበር፡፡ ለታጋዩ፣ ለኢ/ያ ህዝብና ለሌሎች ፖለቲካዊ ድርጅቶች ግን ድንገት ነበር፡፡

ትግላችን ከአማራ ቀኝ ገዥዎች ነፃ ለመውጣት (ነፃ ሪፓብሊክ ትግራይ ለመመስረት) ነው ብለው በትግርኛ፡ በአማርኛ፡ በእንግሊዘኛ የተፃፈ፡ በነ አቶ ስዩም መስፍን ፡መለስ ዜናዊ ፡ ስብሃት ነጋ፡፡ በሙሉጌታ ሓጎስና በሌሎችም የተጻፈ ሥዩም መስፍን ሱዳን ሄደ በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ወደ አገር ገብቶ ለተጋዮችና ለከተማ ደጋፊዎች ለውጭ አገርም እንዲሰራጭ ተደረገ በቃ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ጠባብነት ፀሐይ ላይ ወጣ ፡፡
የዚሁ ማኒፌስቶ በቅድምያ የተቃወመ ኢ.ህ.ኣ.ፖ ነበር፡ ቀጥሎ ትንሽ ቀለም በቆጠሩ ታጋዮችና በከተማ ደጋፊዎች ትልቅ ተቃውሞ አገጠመው ፡፡ ጥያቄ ላነሱ ታጋዮች በተለይ ከ1969 ዓ.ም እስከ 1970 ዓ.ም እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ ብዙ ታጋዮች እየሸሹ ከተማ ገቡ፡፡ ዕድል ያገጠማቸውም ወደ ሱዳን ሸሹ፡፡ትላትና በኢ/ያ የመደብለ-ፓርቲ መኖር አለበት የሚል አÌም የነበራቸው የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በሰሜን ኢ/ያ ለነበሩ ፀረ-ደርግ ኃይሎች መጀመርያ ግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይን (ግ.ገ.ሓ.ት)መቱ፡፡ ቀጥለው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ ጣራናፊት ኮሚቴ አጠፉ፡፡በመቀጠልም የኢ/ያ ዲሞክራሲያዊ ህብረት(ኢ.ዲ.ህ እና ኢ.ህ.ኣ.ፖ) ግዝፎች ኃይሎች ተዋጡ፡ በድርጅቱ ውስጥም ጦርነቱንና ጠባብነቱንና የተቃወሙ፣የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ አይደለም ብለዉ የተማጎቱ ጅግኖቹም እንደዚህ ተዋጡ፡፡ በቃ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ፀረ-መደብለ-ፓርቲና ፀረ-ዲሞክራሲ መሆናቸው ተጋለጠ፡፡ ግን ደግም ፋሽስታዊ ደርግ በትግራይ ህዝብ ጠላትና ወዳጅ ሳይለይ በማከናይዘድ፣ በእግረኛ ወታደር፣ በአየር በጋዝና በናፖልም መርዝ በመጠፍጨፉ ህዝቡ የሩቅ ጀብ ከሚበላኝ የራሴን ጅብ ይብላይኝ በሚል ህዝቡ ዕድሜ ፡ፆታና ሃይማኖት በማይለይ ከህ.ወ.ሐ.ት ጎን ቆሞ ልጆቹ ወደ ትጥቅ ትግሉ እንዲዘመቱ፣ ገንዘቡና በሁሉም ዓይነት ሀብቱ ህ.ወ.ሐ.ትን ለመደገፍ ተነሳ ፡፡
የትግራይ ህዝብ ግን ምንም እንኳን ከደርግ ህ.ወ.ሐ.ት ቢወድም ፡ ህ.ወ.ሐ.ት በጣባብነት አÌሙ የኤርትራን የቅኝ ግዛት ጥያቄ መደገፉ የሻአብያ ካድሬ ሆኖ መንቀሳቀሱ፣ይባስ ብሎ ሻአብያን ከደርግና ከጀብሃ ለመከላከል በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣት ታጋዮች ወደ ሳህል በረሃ በማዝመቱ አምርሮ ይተጋለውና ይቃወመው ነበር፡፡ በዚሁ ተቃውሞ ምክንያት አድመኞች ተብለው እርምጃ የተወሰደባቸው እጅግ ብዙ ፡ አርሶአደሮችና የከተማ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡
የትግራይ ህዝብና የህ.ወ.ሐ.ት የልደት በዓል የካተቲት 11፡-
ከላይ እንደዘረዘርኩት ደርግ ጠላትና ወዳጁ ሳይለይ ይጨፈጭፈው ነበር፡፡ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎችም ያ ጠባብነትና ፀረ-ዲሞክራሲ ባህሪያቸው የህዝብና የተጋዮች ፊት ያሰጋቸው ስለነበር ስግተው ጠባያቸው በመቀየር ብዙ ስለት ይገቡለት ነበር ፡፡ የካቲት 11 የትግል ቀን በመሆኑና ብዙ መስዋእት ስለከፈለበት በዓሉ ሲከበር ከሚወደው አምላክ በማይተናነስ ሁኔታ የየአመቱን በዓል በበለጠ አምልኮት (እምነት) በማሳደር ቤቱ ያፈራውን ሁሉ አይነት የሚበላ የሚጠጣ በመዘጋጀት በሰለማዊ ሰልፍ ልጆቹ በመመልመል ልብስና ቀለብ በመስጠት ወደ ወታሃደራዊ መሰልጠኛ (02) የሚሸኝበት ግዜ ነበር ፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያትም የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በዛን ግዜ ቃል የገቡለት ሰለት ከድተው ራሳቸው፣ ልጆቻቸውና ዘር-መንዘራቸው ሃብት መካበት፣ምርጥ ቪላዎችና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ባገር ውስጥና በውጭ ሰርተው የሃገራችን ዶላር እየዛቁ በውጭ ባንኮች አስቀምጠው ለክፉ ቀን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ያን ግዜ በታጋይነት ጊዜ፣የመሴ ደቀመዝሙር በነበሩበት ጊዜ፤መድረክ ወጥተው በካድሬዎቻቸውና ራሳቸው ሲናገሩ ህ.ወ.ሐ.ት ደርግ አስወግዶ ባጭር ግዜ የህቡን ችግር ይፈታል የሚል እምነት የሚያሳድር ነበር፡፡ ነገር ግን ህወሐት ቃሉና ተግባሩና ለየብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ህዝቡ ልጆቹን መርቆ ለመስዋእትነት ሲልክ የስደት ፡የድህነት፡ የስራ አጥነት ችግሮች መፍትሄ አግኝበታሎህ ብሎ ተስፋ በመጣል ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡና ታጋዩ አንድ ያልተገነዘበው ነገር ነበር፡፡እነዚህ የህወሐት ቁንጮ አመራሮች ማንነት በምንመረምርበት ጊዜ ለህዝብ ጥቅም ለመቆም ምንም ምክንያት(background)የላቸውም፡፡ የነሱ ወደ ትጥቅ ትግል መግባት የአባቶቻቸው ስልጣን አሻሽለው ራሳቸውን ገዥዎች ለመሆን አስበው የተነሱ “ታጋዮች” ናቸው፡፡ ስለሆነም ነው አሁን በመቶ ሺ የወጣቱ መስዋእትነት ስልጣን ላይ ወጥተው የአገር ለአላውነት መደፈር፡ የሰብኣዊ መብት ረገጣ ፡ የህግ በላይነት አለመኖር፣ ባጠቃላይ በአገሪቱ በመድብለ-ፓርቲ ስርዓት፣ የዲሞክራሲያዊ መንግሥት መመስረት የቃል መፈክር ሆኖ እንዲቀር ያደረጉት፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ውድድር ህዝቡ በነፃ የመሰለውን የፖለቲካ ፓርቲ መርጦ መንግሥት እንዳይመሰርት የከለከሉት የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ስልጣን አሳልፈው ላለመስጠት ነው፡፡ የካቲት 11/1967 ዓ.ም በረሀ ሲገቡ ይህንን ድብቅ ዓላማ ከ4 የአንጎላቸው ክፍል በአንዱ ሥር አስቀምጠው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፡፡ በትጥቅ ትግሉ ለህዝብ የቆሙ፣ብቃት የነበራቸው ታጋዮች የአሁኖቹ አመራሮች የአባቶቻቸው የስልጣን ኮርቻ ላይ እንዳይወጡ ስጋት ሁነው ስለተገኙ በትጥቅ ትግሉ እንዲቀጥሉ አልተፈለገምና እንዲወገዱ ተደረገ፡፡ ህዝቡ የካቲት 11 የሁሉም ነገር መፍትሔ ናት ብሎ ያምን ነበር፡፡ነገር ግን የካቲት 11 ደርግ ደምስሳ ሰላም፣ ፍቅር፣ የኢ/ያ አንድነት ማረጋገጥ አልቻለችም፡፡ የ17 ዓመት ሙሉ የትጥቅ ትግል፣የመቶ ሺዎች ወጣቶች መስዋእነት ለፊውዳል ልጆች የአባቶቻቸውና የአቶቻቸው ስልጣን እንዲረከቡ አስቻላቸው፡፡ ህዝቡ የካቲት 11 ሲያ ከብር ቀደም ብሎ ከልቡ በመነጨ ፍቅር ነበር የሚያከብራት፡፡ ሁኔታው ቀስ በቀስ እየተረዳው ሲመጣ ግን ዕለቱን ለማክበር ድርጅቱ ህዝቡን በማስገደድ እንዲያከብር ያደርገው ጀመር፡፡ህወሐት/ኢህአዴግ ስልጣን ላይ የወጣው በኃይል በማሸነፍ እንጂ በሐሳብ በማሸነፍ( defeat not win) ስላይደለ የህዝብ መብቶች ማስከበር አይችልም፡፡

የህ.ወ.ሐ.ት 40ኛ የልደት በዓልና የትግራይ ህዝብ፡-
የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በአፈቀላጤዎቻቸው አማካኝነት ባለፉት 24 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው በኢ/ያ ፍትህ፣ የህግ የበላይነት፣ የዜጎች ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረዋል፣ የብሄር ብሄረሰብ መብት የራስን እድል በራስ የመውሰን መብት ተከብረዋል፡፡ የታገልንበት መደብለ-ፓርቲ ህልውና በኢ/ያ ተረጋግጣል ፡፡ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የእንባ ጠባቂ ኮሚሽን ተÌቁማል፡፡ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተÌቁማል ፡፡ የነፃ የፍትህ አካላት ተመስርተዋል ይሉናል፡፡
በኢኮኖሚም በአለም ደረጃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለመድረስ ተቃርበናል ፡፡ በመሰረተ ልማት፤ በመንገድ፣ በሃድሮ -ኤሌክትሪክ አድገናል ፣ የማይደፈር አባይን ደፍረናል፡፡ የባቡር ሃዲድ እየሰራን ነው፡፡ በቲክኖሎጂ አድገናል፡፡ በእርሻ አድገናል፡፡ የእርሻ ኢንቨስትመት ተስፍፍቷል፡ የመስኖ ስራ ተሰፋፍቷል ፡ ህዝባችን በቀን ሦወስት ግዜ በልቶ እንዲኖር አድርገናል ፡፡ በኢንዳስትሪ ከበለፀጉ አገሮች ተወዳዳሪ ወደ መሆን ደርሰናል፡፡በማህበራዊ አገልግሎት በትምህርት፣ በሕክምና፣ በውሃ ሽፋን በኤሌክትሪክ አገልግሎት ፡ ከነበሩት መንግሥታት በአጭር ዓመታት ውስጥ በበለጠ መሰረታዊ ዕድገት አስመዝግበናል ይሉናል፡፡
በፀጥታና በፍትህ ህዝባችን የተሻለ አገልግሎት አግኝቷል፡፡ የህግ የበላይነት ተረጋግጧል ፡፡ በሃገራችን የተረጋጋና ሰለማዊ ሁኔታ ተረጋግጧል ይላሉ፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና አጃቢዎቻቸው በ40ኛ የልደት በዓላቸው ይህንን ለመሸፋፈን እያደረጉት ያለ ዝግጅት፡-
ህ.ወ.ሃት በአሁኑ ግዜ 40ኛ የልደት በአሉ ሲያከብር ካለፉት 39 አመታት የበለጠ አከባበር ለማክበር እየተዘጋጀ ነው፡፡ለዚሁም ከውጭ አገር (ከዲያስፖራው) ማህበረሰብ ከ100.000 በላይ እንግዶች እንደሚመጡ ከወዲሁ አውጃዋል፡፡ ካገር ውስጥም ከክልል መሰተዳደሮች ተወካዮች ሰቢክ ማህበራት እነዚህም በመቶሺ የሚቆጠሩ እንግዶች ይመጣሉ፡፡ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የትግራይ ተወላጅችም ከእንግዶች ውስጥ እንደሆኑ ተነግረዋል፡ የሃገራችን የኪነት ባለሙያዎች ፀሐፊዎች ከወዲሁ እየተነገራቸው ነው፡፡ በትግራይ ክልልም ከሁሉም ዘኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የተወከሉ እድምተኖች በመቶሺዎች ይጠራሉ፡፡ የመቀሌ ህዝብ ከ300,000 በላይ ተጨምሮበት መቀሌ እጅግ ብዙ ሰው ታሰተናግዳለች፡፡ በተጨማሪ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ እስከ ቤተሰብ ቤት ቁጥር በግድ ያከብራል ሃብትም ይባክናል፡፡

በትራንስፖርት መስከም በሃገራችን ያሉ ምርጥ ኤም.ቢ.ኤም ኮብራዎች አውቶቡሶች ይዘጋጃሉ፡፡ በገንዘብ ሲተመን ለነዳጅ ለታዳሚዎች ውሎ አበል የሚወጣ እጅግ ብዙ ሚልዮን ብር ነው፡፡ በዚሁ በመቀሌ ለእድምተኛች የሚወጣ ገንዘብ በመቶ ሚልዮን የሚገመት ነው፡፡ የአየር መንገድና የመከላከያ ሚንስቴር አውሮፕላኖችም ለዚሁ በዓል ማክበር የፀጥታ ኃይሎች የሃገር መከላከያ ፡ ፌደራል ፖሊስ፡ ድህንነትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊመጡ ናቸው ፡፡ ለዚሁ በዓል ዝግጅትና ምግብ ለመÙÙዝ ከሚያጠፉት የመንግሥት የስራ ግዜ ሳይቆጠር የሚባክነው ገንዘብ በብዙ መቶ ሚልዮን የሚገመት ይሆናል፡፡

ህ.ወ.ሃ.ት የ40ኛ የልደቱ አመት ለማክበር ይህ ሁሉ ወጪ ሲያወጣ ዛሬ ብቻ አይደለም፡፡ ስልጣን ከያዘ ቀን ጀምሮ እስከዛሬ በቢልዮን የሚገመት ሃብት አባክነዋል፡፡ ይህ የማባከን ጉዳይ ግን በህ.ወ.ሃ.ት ውስጥ ታጥሮ የቀረ አልነበረም፡፡ ሌሎች አጃቢ የፖለቲካ ድርጅቶችም የህ.ወ.ሃ.ት ሞዴልነት በመከተል፡ የብአዴን፣ የአሆዲድ፣የዲህዳን ፡ የጋንቤላ፡ የዓፋር ፡ የቤንሻንጉል፡ የሶማል ፡ የሃደሬ፡ በዓላትም እጅጉን አባካኝ ፍፃሜዎች ታይተዋል ፡፡ በተጨማሪ ለግንቦት 20 ብዙ ባክነዋል አሁንም 20ኛ ዓመት ሊከበር ነው፡፡ ይህ ሁሉ በልማት ስራ ቢውል ኖሮ ስንት ድህነት በቀረፈ ስንት ህዝብ ከስደት በዳነ ነበር፡፡ ህ.ወ.ሃ.ት ግን ራሱን ለማዝናናት ይወዳል፡፡ አለማውም ይኸው ነው፡፡በአሁኑ ግዜ በትግራይ ዲግርና ዲፕሎማ የተመረቀ በመቀሌ ብቻ ከ30,000 በላይ ስራጥ ወጣት አለ፡፡ 10ኛ፣12ና 8ኛ ክፍል የወደቁ ተማሪዎች አይቆጠሩም፡፡ ህወሐት ይህ ሁሉ ቢልዮን ብር ለክርስትናው ከሚያጠፋ እነዚህ በትምህርት ጥራት ዕጦት ምክንያት የወደቁ ተማሪዎች ማስተማርና ማብቃት መምረጥ ነበረበት፡፡ነገር ግን የካቲት 11 የህወሐት አመራር ከድሮውም የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ስልጣን ለማስረከብ ቀይሰው የተጓዙበት ዕለት በመሆኑ በብልዮን መሆኑ ቀርቶ ዓቅም የላቸውም እንጂ በትሪልዮን ብር በዓሉ ቢከበርላቸው ደስታው አይችሉትም፡፡

የጥፋት ዝግጅቱና ዓለማው ፡-
40ኛ የህወሐት የልደት በዓል ዋናው ዓላማው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በአሁኑ ግዜ በትግራይ ህዝብ ዘንድ የነበራቸው አመኔታ ጭራሹን ተማጥጦና ተጠልተው እንደምራቅ የተተፉበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡በመሆኑም በዚሁ በዓል ብዙ የውሸት ይዕድገት ድርሳናት ተደርሰው በፎቶግራፍ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በሬድዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በግብዣና በዲስኩር በማደንዘዝ የህዝብን አቅጣጫ በመቀየርና በማላሳለስ የስልጣን እድሚያቸው ለማራዘም እንደልማዳቸው የትግራይን ህዝብ እንደመጠቀምያ ለማድረግ ነው፡፡ ሌላው ዓላማ በ2007 ዓ.ም የፓርላማ ምርጫ ዘመን እጅጉን ስለሰጉ በዚህ በዓል አመካኝተው የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግና የህዝቡ አስተሳሰብ መቀየር፣ የህዝቡን ብሶት ለማብረድ፤ወጣትን የውሸት ታሪክ በመደርደርና በመፈረክ በኘሮፖጋንዳ ለማዳንዘዝና በአጉል የተስፋ መንገድ እንዲቆም ለማደረግ ነው፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት 40ኛው የልደት በዓልና ፋይዳው፡-
ህወሐት የተነሳለት ብሄራዊና መደባዊ ጭቆና በመጣል በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግሥት መመሰረት የሚል ዓላማ ለማሳካት አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎም ከዘውዳዊው ስርዓትና ከፋሽስታዊ ደርግ ስርዓት በባሰ መንገድ ህዝቡን እየጨቆነና እየበዛበዘው ይገኛል፡፡ህዝቡ የድሮ የበሰበሱ በዝበዥ ስርዓቶች አስወግዶ፡ 17 ዓመታት ሙሉ ታግሎ የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው አሮጌውን ስርዓት አሳድሰው ህዝቡን በዘመናዊ መንገድ የሚጨቁኑ ገዥዎች አፍርተዋል፡፡

ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶቹ አልተከበሩለትም፡፡ የየካቲት 11 ውጤት ይህ መሆን ነበረበት፡፡ ህዝቡ ደርግን ማስወገድ ብቸኛው መፍትሔ ይመስለው ነበር፡፡የካቲት 11 ገዥዎች ነቅላ ሌሎች ገዥዎች ታመጣለች ብሎ ህዝቡ አስቦ አያቅም ነበር፡፡ ሀቁ ግን ይህ ሆኖ ቀረ፡፡ የካቲት 11 አደራ በልተሻል ብለው ለተቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ታስራለች፣አገር ለቀው እንዲሄዱ እያደረገች ነው፡፡ የካቲት 11 ያ ሁሉ ወጣት በጉያሽ አቅፈሽ፣ለክብርሽ መስዋእት ሆኖ ለአዲስ ገዥዎች አሳልፋ መስጠቷ በየካቲት 11 ያገኘነው ነገር ካለ ልጆቻችን መስዋእት መሆናቸው እንጂ የፈየደችን ነገር የለም እያሉ ናቸው፡፡ የካቲት 11 ይህ ሁሉ ወጣት በልተሽ ለጥቂት የገዥ መደብ ልጆች ጥቅም መቆምሽ ከበደል በደል ነው፡፡

የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ሲከበር እኛ ህዝቦች ከደርግ መንግሥት የዜሮ ዲሞክራሲ ወጥተን በራሳችን ፍቃድ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላውነት ተከብሮ እርስ በራሳችን ተፋቅረን እንኖራለን ብለን ነበር፡፡ በ40ኛ ዓመትሽ በህወሐት/ኢአዴግ መንግሥት እርስ በራሳችን ብጥርጣሬ ዓይን እንድንተያይ፣አንዱ በሌላው ክልል ሄዶ ሰርቶ የመኖር ዕድል ዘግቶ ይገኛል፡፡ እርስ በራሱ እንደጠላት እንዲተያይ እየተደረገ ነው፡፡ ደርግ ሃይማኖት ለማጥፋት ሲጥር ህወሐት/ኢህአዴግ ደግሞ በሃይሞት ነፃነት ጣልቃ በመግባት እርስ በራሳችን የነበረንን የመከባበር እሴት በማደፍረስ አንድነታችንን እንዲላላ በማድረግ ለፖለቲካ ፍጆታው እያዋለው ይገኛል፡፡
ደርግ ዜጎች የመደራጀት፣የመናገር፣የመጻፍ መብት የከለከለ መንግሥት ስለነበር እኛ የጊዜው ወጣቶች ታጥቀን ደርግን እንድናስወግደው ያንችን ጥሪ ሰምተን ታግለናል፡፡ ውጤቱ ለዚህ ብለን አልነበረም፡፡ የፊውዳል ልጆች የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ሥልጣን ለማስረከብ ብለን አይደለም ደደቢት የወጣነው፡፡

የካቲት 11 አሁን 40ኛ ዓመትሽ እየተከበረ ነው፡፡ እርግጥ ነው ጤና እንዳላገኘሽና በአከባብያችን እንደሌለሽ ይገባናል፡፡ ከአጠገባችን ብትኖሪ ኖሮ ይህ ሁሉ ግፍ ብህዝቡ እየወረደ ዝም ብለሽ ማየት እንደማትችይ ይገባናል፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች መሬት ላራሹ፣ የከተማ መሬት በነፃ ለህዝብ በእኩልነት ይታደል ብለው የታገሉና ለህዝብ አነስስተው ደርግን ለመጣል ያስቻላቸው የመሬት ጥያቄ በመክዳት፣ መሬት የመንግስት ናት በማለት የከተማና በከተማ አካባቢ የሚገኙ የህዝብ መሬት በመቀማት በመሸጥ ለራሳቸውና ለዘር መንዝራቸው የሃብት ምንጭ አድርገውታል ፡፡ የገጠር መሬት የህዝቡን ባለቤትነት በመንጠቅ በአርሶአደሩ የማልማት ዓቅም ለሌላቸው ግለሰዎች በመሰጠቱ ወጣት አርሶ አደር የወጣት ጥንቻው ሊያሳርፍበት የሚችል መሬት ባለማግኜቱ ጉሳሳ ጎጆ ሰርቶ የሚተኝበት መሬት ተከልክሎ በረሃና ባህር ተሸግሮ ወደ ስደት ፈልሰዋል ፡፡ በአንፃሩ የህ.ወሃ.ት መሪዎችና ልጆቻች ባገር ውስጥና በውጭ ሰማይጠንቀስ ህንፃዎች ሰርተው የሚኖርበት ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡
የካቲት 11 40ኛ ዓመት የልደት በዓልሽ ስናከብር ይህንን ጉድ ተሸክመን ነው፡፡ግን የካቲት 11 ልጠይቅሽ እነዚህ ቱጃሮች ለመፍጠር ነበር የትግሉ ዓላማ?

አይደለም ፍፁም አይደለም ፡፡ በኛ በኩል አስበነውም አናቅም፡፡እነሱ ግን ይህንን ዓልመው ይጓዙ ስለነበር ያሰቡትን አሳክተዋል፡፡ የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ስናከብር በሃዘን መሆኑ ማወቅ አለብሽ፡፡ ምኞታችን የነበረው በ40ኛው የልደት በዓልሽ ገጠሪቷ ትግራይ ከ13 ዓመት ዕድሜ በላይ ወጣት የማይኖርበት፣ በገጠር ህፃን፣ ሽማግሌ ከሞተ ሬሳ ተሸክሞ ወደ መቃብር የሚወስድ ወጣት ይጠፋል ብለን ኣናስብ ነበር ግን ሆነ ፡፡ የገጠር ወጣቱ አብዛኛው ወደ ጎረቤት አገሮች ሲሰደድ የቀረው ወጣት ወደ ክልል ከተሞችና አዲስአበባ ፈልሰው ከተሞችን አጣብበዋል ፡፡ ሴት እህቶቻችን ባገር ውስጥም በውጭም ካለፉት ስርአቶች በባሰ ለዝሙት ስራ ተጋልጠው እየተዋረዱ ይገኛሉ ፡፡ ለመጥፎ በሽታ ተጋልጠዋል፡፡ የገጠር ሴቶች ባሎቻቸው ወደ ስደት በመፍላሳቸው ህፃናት ይዘው በሃገር ቤት በረሃብ በበሽታ ይሳቃያሉ፡፡ የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ስናከብር ይህንን ስቃይ እያየን ነው፡፡

በከተማ ያለው የተማረና ያልተማረ ወጣትም በስራ አጥነት ምክንያት ለፀጥታና ለሰላም ጠንቅ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለይ በዮኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ወጣቶችም በመጥፎ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡ ያቺ እንደ እሳት አደጋ ማጥፈያ የሚጠቀሙላት ከቡልስቶን በከተማ አስተዳደሪዎች፣ ከንቲባዎች በሙስና ተመዝብረው ተማሪዎች ከስረዋል፤ ምሳሌ ለመጥቀስ በመቀሌ ከተማ 29 ማህበራት 800 አባላት ያቀፈ ማህበር ሰባት ማህበራት የተወሰነ ትርፍ ሲያገኙ 22 ማህበራት ከስረዋል፡፡ ከመክሰር አልፈውም፡ በእዳ ተይዘው በየ ፍርድቤት እየተንከራተቱ ይገኛሉ፡፡ ከትምህርት ጥራት አለመኖር ተያይዞ በትግራይ 8ኛ፣10ኛና 12ኛ ክፍል ከትምህርት የወደቁ ወጣቶች እጅጉን ብዙ ናቸው፡፡የየካቲት 11 40ኛ ልደት ዓመት ስናከብር ይህንን እያየን ነው፡፡
እነዚህም ከትምህርት ከራቁ የሚሰሩበት ቦታ ባለመኖሩ ለቦዘኔነትና ለተለያዩ ሱስ የተጋለጡ ናቸው፡ ትግራይ የጦር አካል ጉዳተኞች መንደር ሆናለች፡፡ በትግራይ ብቻ ከ126 ሺ በላይ አካል ጉዳተኞች አሉ፡፡ከነዚህ እጅግ ጥቂት ሰዎች አብዘኞቹ ከ500 ብር በታች ጥሮታ አላቻቸው የቀረው አያገኝም፡፡ አኗኗሩ እጅጉን የከፋ ነው፡፡ የተሰው ታጋዮች ወላጆች ብዙዎቹ አርጅተው ወይም በሀዘን ሲሞቱ አብዛኞዎቹ ጧሪ አጥተው የሚሰቃዩ አሉ፡፡ በትጥቅ ትግል ግዜ በሚልሻነት ፡ በገጠር ካድሬነት ያገለገሉ በአሁኑ ግዜ የጡሮታ ይሁን ሌላ ገቢ ስለሌላቸው በድህነት የተÌራመቱ ናቸው፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የእነዚህ “ነዳያን” ህይወት አይፈልጓትም፡፡መሪዎቹ አንድ ጭንቅ ሲያጋጥማቸው ብቻ መጠቀምያ ለማድረግ በውል አበል ይሰበስቧቸዋል፡፡ይህ ሁሉ በሕ/ሰቡ የከፋ ድህነት እያለ ከአፍንጫቸው ውጭ አርቀው የማያስቡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በመቶ የሚገመት የህዝብ ሃብት ለመባከን ተዘጋጅተው ይገኛሉ፡፡
የካቲት 11 በስምሽ ላንች ብለው በረሃ ወጥተው መስዋእት ሁነው ወላጆቻቸው በከፋ ድህነት እያሉ በስምሽ የህወሐት መሪዎች ይህ ሁሉ ቢልዮን የህዝብ ሀብት አውጥተው ሊዝናኑ ፍቃደኛ እንደማትሀኝ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም፡፡ ከዓቅምሽ በላይ ሆኖ ልብሽ እየደማ ከኛ ጎን እንዳለሽ እንረዳለን፡፡

የዛሬው አያደርገውና ህወሐት ደርግን ከህዝብ ለናት አገር ጥሪ እያለ ገንዘብ በኃይል ይሰበስባል እያለ ይከሰው ነበር፡፡ ህወሓት በ40ኛው የልደት በዓሉ የደርግን መዋጮ በከፋ መልኩ ሲደግመው እንመለከታለን፡፡ የክፍያ ዓይነቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዳንዶቹን ለመጥቀስ፡-
1. የአባልነት፣ለዓባይ፣ለማህበር ልማት ትግራይ፣ለአዲስ ራእይ መፅሄት፣ለመለስ ፋውንዴሽን፣ለመለስ ኣካዳሚ፣ለወጣቶች፣ሴቶች ማህበር የመከፈል የወር ክፍያ፣የጋዜጣ ወይን ክፍያ፣፣ ከያንዳንዱ ኔት ወርክ በወር 70 ብር ይከፈላል፡፡ በአንድ ወረዳ ቢያንስ 600 የልማት ብዱን አለ፡፡ ከነዚህ 70 ብር በወር 42000.00 ይሆናል፡፡ በትግራይ ክልል 52 ወረዳዎች አሉ ከነዚህ ወረዳዎች አነስተኛውን የልማት ብዱኑ ቁጥር ወስደን ብናሰላዉ በጣም ብዙ ገንዘብ እየሰበሰቡ ህዝቡን እመዘበሩ መሆናቸው ግልፅ ነው ፡፡ደርግ ይህን ያህል መዋጮ አልነበረውም፡፡ ያው የምትታወቀው በዓመት አንድ ጊዜ የእናት ሀገር ጥሪ ነበረች እንጂ፡፡

ማህበራዊ አገልግሎትና 40ኛው የህወሐት የልደት ዓመት፡-
በ40ኛው የህወሐት የልደት በዓል የህክምናው አገልግሎት ዘርፍ ሲታይ ብዙ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣብያዎች፣ ክንሊኮችና ጤና ኬላዎች ተገንብተዋል፡፡ነገር ግን ህጻቸው ነው እንጂ ብቁ የኅክምና ባለሞያና መድኃኒት አይገኙባቸውም ከተገኘም ከ5 ዓይነት መድሃኒቶች አንዱ እንኳ የተሟላ አይደለም፡፡ ድሆች ታመው ሄደው የሚታከሙባቸው አይደሉም፡፡ለሌላ ህክምና ሪፈር የተባሉ ዜጎች የድህነት ወረቀት ካመጣቹህ በነፃ ትታከማላቹህ ይባሉ እንጂ በሪፈር ተልከው ለመታከም በየደራጃው ያሉ ነብሰ በላ-አስታደሮች ጉቦ ሰጥተው ያሰቡትን ለመድረስ ሳይችሉ የቀሩና በህክምና እጦት እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎች፣የጦር ጉዳተኛች በጣም ብዙ ናቸው፡፡የሪፈር ወረቀት ለማግኘት በቀበሌና በወረዳ አስተዳዳሪዎች መፅደቅ አለበት፡፡ወረቀቱ ለማየት በስብሰባ ላይ ነን ብለው ወረቀቱን ለወራት ውሳኔ ሳያገኝ ይቆያል፡፡ጉዳዩ ግን የፍርድ ጉዳይ ሳይሆን የህይወት ገየዳይ ነው የፍርድ ውሳኔ ማዘግየትም የሚበረታታ ባይሆንም፡፡ እነዚህ ችግሮኞች የሚታከሙት ከወረዳው በጀት ስለሆነ ወረዳ አስተዳዳሪው ከኪሱ እንደወጣ ብር ሆኖ ስለሚሰማው እነሱን ከማከም የተለያዩ ምክንያቶች በመደርደር በሃብታሞች ሆቴል አምሳያዎቹን ጠርቶ በቁርጥና በቢራ ለመዝናናት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቡ ተስፋ ቆርጦ ህክምና ከመሄድ ፈንታ ወደ ደፍተራ፣ ጠንቃይ እምነቶች እየተንከራተተ እያለ ሞት ይቀድመዋል፡፡በአንፃሩ በካቲት 11 ምክንያት ስልጣን ላይ የወጡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ልጆቻቸው ግን ጉንፋን እንኳ ቢታመሙ በዘበናዊ አውሮፕላን ውጭአገር በመክነፍ ዘመናዊ ሙቀት ቀምሰው ይመለሳሉ፡፡የትራንስፖርት ይሁን የህክምናው ወጭ ከመንግሥት ካዝና ነው፡፡ሒሳቡ ሲወራረድ ለኢንቨስትመንት ሄደው ተብሎ ይያዛል፡፡ ሰርግ ላይ ነበሩ ቢባልስ ማን ጠያቂ አላቸውና ነው፡፡የካቲት 11 40ኛው የልደት ዓመትሽ ስናከብር በዚሁ ሁኔታ ሁነን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎችና ስርወ-መንግሥታቸው ጥዋትና ማታ በደቡብ አፍሪካ፡ በታይዋን ፡ በዱባይ ፡ በጀርመን ፡ በበልጄም፡ በእስራኤል ፡ በአሜሪካና በእንግሊዝ ፊታቸው ጦቆር ብሎ ከታያቸው በነዚህ አገሮች ሆስፒታሎች ሄደው ቅባት ተሸክመው ይመለሳሉ፡፡ ይታከማሉ ፡፡በህዝቡና በመንግሥት ባለ-ሥልጣናት መካከል ያለው ልዩነት እንግዲህ ይህን ያህል ርቀት አለዉ፡፡የካቲት 11 40ኛው የልደት በዓልሽ የምናከብረው ይህንን ርቀት በጥልቅ ሀዘን እያስታወስን ነው፡፡

በትምህርት መለክም ፡የትምህርት ፖሊሲ ትውልድ ገዳይ ሆኖ እናኘዋለ፡፡ የአስተማሪዎች ክብርና አያያዝ እጅግ ዝቅ እንዲል በመደረጉ፣ ደመወዙ አንስተኛ መኖርያ ቤት የሌለው ፡ በድህነት ምክንያት ማህበራዊ ኑሮ መመሰረት ያልቻለ፣ ተማሪ የአስተማሪውን የተጎሳቀለ ኑሮ እየተመለከተ እሱም የሱ ዕጣፈንታ እንደሚደርሰው በመገንዘብ ለትምህርት የሚሰጠው ትኩረት በማነሱ ምክንያት በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ላይ መድረስ አልቻለም፡፡ በሌላ በኩል የአሰተማሪዎች ብቃት በትምህርት ብቃታቸው ሳይሆን ለገዥው ፓርቲ ባላቸው ታዛዥነት በመሆኑ፣ የፖለቲካ ታማኝነታቸው በመሆኑ፤ታማኝ ለመሆን ደግሞ ተማሪውን በትምህርት መገንባት ሳይሆን ብዙ ተማሪ በኔት ዎርክ በማደራጀት ከገዥው ፓርቲ ስሜትና ቁጥጥር ውጭ እንዳይሄዱ ስለሆነ አስተማሪው ብቁነቱ በዚህ ተመዝኖ ደካማና ጠንካራ ይባላል፡፡ልጆቹን ለማሳደግ ብሎ የተማሪዎችን በኔት ዎርክ ወጥመድ አስገብቶ ንቁና ለአገራቸውና ለህባቸው ሳይሆን የገዥው ፓርቲ ሱሰኞች እንዲሆኑ እየሰራ ይገፃል፡፡ የተማሪዎች ብቃት የሚለካውም በገዥው ፓርቲ ላይ ባላቸው ሱሰኝነት ነው፡፡ አስተማሪው ከአስተማሪነት ወጥቶ ወደሌላ የተሻለ ሥራ ሊሰማራ ከሆነ የብቃቱ መመዘኛ ምን ያህል የተማሪዎች ኔት ዎርክ መሰረተ ነው እንጂ በትምህርት ብቃቱ አይደለም፡፡

በሌላ በኩል ከክልሎች ዮንቨርስቲዎች ተመርቀው የሚወጡ ምሩቃን ወደ ልማት ተሰማርተው ለመስራት የሚያስችል ፕሮጀክት ስለሌለ ከዩንቨርስቲ ሲወጡ ሞራላቸው ይወድቃል፡፡ በተጨማሪ ከዩንቨርስቲ የሚዎጡ ሙሩቃኖች ዓቅማቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ወጥተውም ከነዛ ባለስልጣኖችና አጋሮቻቸው ልጆች በልዩ ትምህርት ቤት ከመዋእለ ህፃናት እስከ 12ኛው ክፍል የተማሩ ተወዳዳሪዎች ሆነው አይገኙምም ፡፡ በመሆኑም ህወሐት እንደሚለው ከህወሓር ጋ መጭው ብሩህ ነው ሳይሆን አባቶቻቸው ወላጆቻቸው ህዝባችን ገዝተው እነዘጂህም እኛን ገዝተው ልጆቻቸው ግሞ ልጆቻችን እንዲገዙ ሁኔታው እያመቻቹ ይገኛሉ፡፡ የካቲት 11 40ኛው የልደት በዓልሽ ስናከብር ይህንን እየተመለክት ነው፡፡

በድርቂ ምክንያት የሚመጣ በድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት፣ በአረጋውያን ስም፣ በኤች.አይ.ቪ ስም፣ በአካል ጉዳተኞች ስም፡ በሴፍትነትና በትግራይ ረዲኤት ማህበር ስም የሚመጣው ዕርዳታ ማግኘት የሚቻለው ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን በፖለቲካ አመለካከት ላይ መሰረት ተደርጎ ነው፡፡ህወሐትን የሚቃወም በከፋ ችግር ላይ ቢወድቅ የዕርዳታው ተቋዳሽ የሚያደርገው የለም፡፡ዕርዳታው ለማግኘት የመጀመሪያው መስፈርት ህወሐትን ያመልካል ወይስ ሌላ አመለካከት አለው ተብሎ ህወሐትን ይቀበላል ተብሎ ምስክርነት ከተሰጠው በኋላ ነው ዕርዳታው የሚሰጠው፡፡የሚገርመው ነገር ግን በበሽታ ምክንያት አልጋ ላይ የወደቁ ሽማግሌዎችም በዚህ መስፈርት ማለፋቸው ነው፡፡ ህወሐት ወጣቱን ብቻ አይደለም የሚፈራው አሮጌውም፣ህፃኑም ወጣቱም ጭምር ነው፡፡ ይህ በመሆኑክ የህ.ወ.ሃ.ት አባል አልሆንም ያለ አሮጌ ወይም አካል ጉዳተኛ ዕርዳታው አያገኝም ፡፡ንፁህ የሚጠጥ ውኃ ችግር በትግራይ ክልል ባለፉት የየካቲት 11 ዓመታት እንደተፈታ ህወሐት እየነገረን ነው፡፡ በትግራይ ክልል በተለያየ ግዜ የውኃ ሽፋኑ አንዴ 90% ሌላ ግዜ 63% ተጠቃሚ ሆነዋል ይለናል፡፡ ነገር ግን የሚባለው ሁሉ ውሸት ነው፡፡ ያለው ችግር ለመግፅ ይቻላል ፡፡ የመቀሌን የውኃ ችግር ሞዴልነት መግለፅ በቂ ነው፡፡መቀሌ ከ300.000 ህዝብ በላይ የሚኖርባት የክልሉ መዲና ናት፡፡በመሆኑም በተለያዩ አቅጣጫዎች በቀን ከ10.000 በላይ እንግዳ ይገባል ፡፡ ነዋሪው ህዝብ በወር በሁለት ሳምንት ብቻ አንድ ግዜ ውኃ ያገኛል፡፡ ሆቴሎች ምግብ ቤቶች አብዛኛው ግዜ ውኃ የላቸውም ፡፡ችግሩ ለህዝቡ ነው እንጂ ለህወሐት ቱጃሮች እማ የታሸገ ውኃ ከነቤተሰቦቻቸው በመንግሥት በጀት ቤታቸው ድረስ በመኪና ተጭኖ በየደቂቃዎች ይቀርብላቸዋል፡፡ እውነታቸው ነው የህዝቡን የውኃ ችግር ሊረዱት አይችሉም፡፡ሃብታም የረሀብን ስቃይ አይረዳውም ይባል የለም፡፡ህዝቡ ለምን ይራባል ብስኩት አይሰጡትም ዓይነት ነው፡፡

በሽሬ ከተማ ከ80ሺ ህዝብ በላይ አለ፡፡ የሽሬ ህዝብ ህ.ወ.ሃ.ት ከገባ ውኃ አላገኘም ፡ በወር አንድ ሳምንት ብቻ በጥቂት አከባቢዎች ውኃ ያገኛል፡፡ የውኃ ችግር ስላለ በሆቴሎች ለመተኛት እጅግ ብዙ ችግር እየተከሰተ ይገኛል ፡፡በሌሎች የዞን ከተሞችም ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ ምናልባት የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በመጭው 40ኛው ዓመት ልደታቸው ሲያክብሩ የእንታይ እንታይ ባህሪ ስላላቸው ለእግረ መንገዶቸው ውኃ በቦቴ አምጥተው ያጠጡን ይሆናል፡፡ እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩ በትግራይ ያሉ ችግሮች በዝርዝር ለመግለፅ ተሞክረዋል፡፡ነገር ግን አንድ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ አለ፡፡ እሱም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች 40ኛው የልደት በዓላቸው ለማክበር በመቶ ሚልዮን የሚገመት ብርና ዶላር ለመርጨት ተዘጋጅተዋል፡፡ ፍላጎታቸው ምን ይሆን ? ባለፉት 24 ዓመታት ህ.ወ.ሃ.ት የካቲት 11ና ግንቦት 20 ለማክበር በህ.ወ.ሃ.ት ብቻ በቢልዮን የሚገመት ገንዘብ ባክነዋል፡፡ ሌሎች አጃቢ አጋር ፓርቲዎች የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሌጋስ በመከተል ብዙ ሃብት አባክነዋል ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለህዝብ የሚያስቡ ከሆነ የፓርቲዎች የልደት በዓላት ለተሰው ወገኖች በየአሉበት ዝክረ ሰማእታት አድርገው ታስቦ ቢውልና በሚድያዎች ቢነገር እና በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብና ቁሳቁስ ለድህነት ማጥፍያ ቢውል ምን አለበት፡፡ በ1977 ዓ.ም ደርግ 10ኛ የአቤዮት በዓል ለማክበር በ10 ሚልዮን ብር ዊስኪ ከእንግሊዝ አገር አስመጥቶ ግብዣ አድርገዋል በማለት ህወሐት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ተጠቅሞበት ነበር፡፡ ታድያ የህ.ወሃ.ት መሪዎች በ10 ሚልዮን ብር መጥፋቱ እየተቆረቆሩ ቆይተው አሁን ከደርግ እጅግ የበለጠ ማበከናቸው የሱን ተግባር መድገም አይደለም ትላላቹህ፡፡ በኔ እምነት በአሁኑ ግዜ ህዝባችን በመጥፎ ሁኔታ እያለ በመቶዎች ሚልዩን ብር ለማባከን መዘጋጀቱ የኢ/ያ ህዝብ በተለይ በቅርብ ይመለከተው ያለው የትግራይ ህዝብ እንዲቆም መጣር አለበት፡፡ በአሁኑ ግዜ ህ.ወ.ሃ.ት የሚባል ፓርቲ ለስም ነው እንጂ በህይወት ያለ አይመስለኝም፡፡አለ ካላቹህ ደግሞ 40ኛ የልደት በዓሉ እናክብራለን ካላችሁ ገንዘቡ ለድሆች መቋቋሚያ ውሎ በዓሉ በያለበት በሻይና በንፍሮ ብዙ ሀብት ሳይባክን ቢከበር መልካም ነው፡፡ አለበለዝያ ህዝቡ መቃወም አለበት፡፡ ለዚህ ብክነት ሙሁራኑ ተማሪዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ አርሶ አደሮችና አባቶች በመሬት መቃወምና ሁኔታውን ወደ ጥሩ ሁኔታ እንዲቀለበስ መጣር አለባቸው፡፡

የትግራይ ምድር በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች እጅ በመውደቁ በከተማው የሚነረው የመንግሥት ስራተኛና ነዋሪው ህዝብ በመጠልያ ችግር እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ ህ.ወ.ሃ.ት ቀደም ሲል መሬት የከተማና የገጠር የህዝብ ብቻ ነው ሲል ቆዩቶ አሁን ደግሞ ህዝቡን ለማታለል መሬት የመንግሥትና የህዝብ ነው ይለናል፡፡ በመጨረሻው ህ.ወ.ሃ.ት መሬት የመንግሥት ብቻ ነች ብሎን ቁጭ አለ፡፡ 90 ሚልዮን የኢ/ያ ህዝብ የመንግሥት ጢሰኛ ነህ ብሎን ቁጭ አለ ፡፡ እንዳውም መሬት የህዝብ መሆን አለበት ለሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህወሐት መሬት የህዝብ የምትሆነው በኔ መቃብር ብቻ ነው አለን፡፡ እውነታቸው ነው የአባቶቻቸው ዱካ ተከትለው እየሄዱ አይደል፡፡ መስንነትን ዘመናዊ በማድረግ ስልጣን ላይ መቆየት ነው ዓላማቸው፡፡
መሬት የመንግሥት በመሆኑ በየቀበሌው ቤት እያሰሩ የሚገኙ ጥቂት ሃብታሞችና የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በመሆናቸው ነው፡፡ብዙሃኑ ህዝብ ቤት መስራት ስላልቻለ በትግራይ የህ.ወሃትና የጥቂት ግብረ አቦሮቻቸው የሆኑ ጥቂት የኮንስትራክሽን ስራ የሚሰሩ ካለሆኑ በስተቀር የኮንስትራክሽን ስራዎች በመቆማቸው የህንፃ መሳርያ ብረታብረት የሳኒተርና የኤሌክትሪክ እቃዎች ወ.ዘ.ተ ገበያ አጥተዋል ፡፡ ግንበኞች፣ አናጢዎች፣ ለሳኞች፣ የቀን ሰራተኞችና ኮንትራክተሮች ስራ አጥተዋል፡፡ የብረታብረትና የእንጨት ሥራ የሚሰሩ እንዲሁም የቤት ውስጥ ፈርንቸር የሚሰሩ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት (እንድስትሪ) የሚባሉ ከስመዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ ሞያተኞችና ተቋማት ወደ ማኸል አገርና ደቡብ ሱዳን ፈልሰዋል፡፡ በአጠቃላይ በትግራይ የከንስትራክሽን ስራ አሸቆልቁላል፡፡ ተዘማጅ የሆኑ የንግድ ተቋማትም እንደ የምግብ ቤት፣ የልብስና ሌሎች የንግድ ስራዎችም ተዳክመዋል፡፡ በመቀሌ ብዙ የንግድ ቤቶች ተዘግተዋል፡፡የሚካራይ ቤት የሚል ፅሁፍ ተለጥፎ ይታያል፡፡ ነጋዴዎች ከስረው ንግድ ቤታቸው ስለዘጉ ነው፡
የህ.ወ.ሐ.ት 40ኛ የልደት በዓልና የኑሮ ልዩነት፡-
የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች መጀመርያ ወደ ትጥቅ ትግል (ዳፈጣ ውጊያ) ሲጀምሩ አቋማቸው የዘውዳዊው ስርዓትና ፋሽስታዊ የደርግ ስርዓት ያልተመጣጠነ አ••ር፣ ብልሽው አስተዳደርና ሙስና ለማስወገድ ዋነኛው ዓለማችን ነው ብለውን ነበር፡፡ ይህንን መፈክር ያ ሁላ ወጣት መስዋእት ማስከፈሉን በመርሳት የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ደርግ ከተወገደ ሳምምንታ ሳያስቆጥሩ በሙስና ከብዙሃኑ ህዝብ ጋር ያልተመጣጠነ አ••ር አንድ ብለው ጀመሩት ፡፡ያልተመጣጠነ አ••ር ባጭር ግዜ ወዶቻቸውና የካድሬ መዋቅር በመዘርጋት ሀብት በማካበት ቤት መርጦ መያዝ ፡ መኪና መምረጥ ተጀመረ፡፡ ረጅም ሳይÙዝ የዘውዳዊው ንጉሳዊ ቤተሰብ ቅርፅ ይዞ እያቆጠቆጠ መጣ፡፡ ብድብቅ ህንፃዎች መስራት ጀመሩ፡፡ አንድ ሁለት ሦወሶት ህንፃም መያዝ ጀመሩ፡፡ በግልፅም ምርጥ ምርጥ ቦታዎች በጉልበታቸው ያዙ፡፡ ሙሱና በህ.ወ.ሃ.ት መንደርና አጃቢዎቻቸው ህጋዊ መዋቅር ሆነ፡፡ንጉስ የማይከሰስ ሰማይ የማይታረስ ሆነ፡፡ እነሱና የነሱ “ባለሀብቶች” የማይከሰሱ፡ የማይታሰሩ፡ እነሱን የማይጠይቅ ሕግና የሕግ ባለሞያዎች አፈኑ፡፡ የአለም ባንክና አይኤምኤፍ እንደረጋገጡት በ10 ሚልዮን የሚቆጠር ዶላር በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጭ ውጥቷል፡፡ ህዝቦች በስደት በስራ አጥነት እየተሳቃዩ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና አጃቢዎች ፓርቲዎች የሃገራችን ሀብት እየዛቁ ከነልጃቻቸውና ዘመዳቻቸው በአውሮፖና በአሜሪካ ባንኮች እያስቀመጡ ይገኛሉ፡፡ ሚስቶቻቸው ሲያረግዙ አሜሪካና እንግሊዝ አገር እየወሰዱ እንዲወልዱ ይደረጋል፡፡ይህ ተግባር በዘመነ ደርግ እንኳ የሚደረግ አልነበረም፡፡

በዚሁ የ40ኛ የልደት በዓል ዋዜማ ሙስና የስርዓቱ ዋነኛ መለያ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም ህ.ወ.ሃ.ት ከጅምሩ ፀረ-ዘውዳዊ አጋዛዝ አልነበረም ፡፡ ቢሆን ንሮ ደርግ እንደተወገደ በሳምንታት ውስጥ ወደ ሙስና አዘቅት አይገባም ነበር፡፡

የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚባል ሙስና እያጋለጠ ወደ ህግ የሚያቀርብ ብዙ ካድሬዎችና የህግ ባለሞያዎች ያሉበት አንድ ትልቅ ፅፈት ቤት አቋቁሟል፡፡ ይህ ፅፈት ቤት ሙስና የሚያጋልጥ ሳይህን ሙስና የሚያስፋፋ እንደሆነ ነው ህዝብ የሚያውቀው ፡፡አንዳ አንድ ግለሰዎች በመካከለኛ የስልጣን እርከን የነበሩ የኢ/ያ ህዝብ በሙስና የተባላሹ መሆናቸው የሚያውቃቸው በመሆኑ ህ.ወ.ሃ.ቶች ተሸፍኖ የማይሸፈን ሆኖባቸው ፡የህዝብን ስነ-ልቦና ለመቀልበስ ጥቂት ሰዎች ህግ ፊት እንዲቀርቡ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ግን የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ፀረ-ሙስና በመሆናቸው የተወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም፡፡ በመሆኑም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በሙስና ቴክኒክ እጅግ የተካኑ ናቸው፡፡ከዘውዳዊው ስርዓትና ፋሽስታዊ ደርግ የመጠቁና በሙስና የተባላሹ መሆናቸው ፀሐይ የአደባባይ ምስጢር ሆኖዋል፡፡ የ40ኛ የህ.ወ.ሃ.ት መሬዎች ልደት በዓል አለአስፈላጊ ወጭዋችን በመመደብ ሙስና ለመስራት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህ የጥፋት እቅድ አሁንም ይቁም ገንዘብ ለድህነት ማጥፍያ ይዋል፡፡ስራ-አጥ ህዝብ መቃወም አለበት፡፡

በህ.ወ.ሃ.ት ዘመነ አገዛዝ ትግራይ በእርሻና በተፈጥሮ ሃብት ውጤት የትግራይ ክልል መሪዎች በየመድረኩ እየወጡ ተከፍሰው እንደ ሚናገሩት አይደለም ፡፡ እርሻን ብንመለከት አንዳ አንድ መሻሻል ቢኖሩም በተለይ በመስኖ ልማት እጅጉን ስለአደግን እርሻ መርሀ የሚል የኢኮኖሚ ፖሊሳችን ወደ አግሮ እንድስትሪ ተሽጋግረናል እያሉ የሚናገሩን ከሃቅ የራቀ ውሽት ነው፡፡

የህወሐት 40ኛ የልደት ዓመት በዓል ሲከበር የእርሻው ክፍለ-ኢኮኖሚው ህዝባችንን ሊመግብ የማይቻል፣ አርሶ አደሩ ከየካቲት እስከ መጋቢት ወር በቤቱ እሚበላ እሚላስ የሌለው ከ45% በላይ ህዝብ በስፍኔት የሚመገብ ነው፡፡ከላይ እንደጠቀሰው ወጣቶች ሴትም ወንድም ተሰደዋል ፡፡ የእርሻ ውጤቱ ለህዝብ ከረሃብ ያድነው አልቻለም ፡ አርሶአደሮች በቴሌቪዥን የሚናገሩት ውሸት ነው፡፡ ተናገሩ ሽልማት ይሰጣችኋል እየ ተባሉ ነው የሚገገሩት ፡፡ ውሸት መሆኑ በቴሌቭዥን ሀብታሞች ሆነናል ብለው ከተናገሩት አርሶ አደሮች ሳይቀሩ ከሚድያ ውጭ ሲሆኑ ሀቁን ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡ በተፈጥሮ ሃብት ነባር እፅዋት በመንከባከብ በአፈርና ውሃ ጥበቃ እጅግ ብዙ ተሰርቷል፡፡የወደሙ እፅዋቶች በሚመለከት በአሰር ሚልዮን የሚቆጠሩ እፅዋት ይተካላሉ ከተተከሉ ግን 5% ያክልም አይፀድቅም፡፡ ሙከራው መልካም ነው፡፡ በሌላ በኩል የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ተመራማሪዎች ያልተሳተፉበት ፡ በሃገር ደረጃ ያልታወቀ ምርምር እናካይሂዳለን ብለው በግብተዊነት ተነሳስተው በተፈጥሮ ሃብት ብዙ ውድመት ፈፅመዋል፡፡ እንደማስረጃነት ለማቅረብ በትግራይ ክልል፣ በደቡብ፣ በደቡብምስራቅና በማእከላዊ ዞን ወረዳዎች ከ2.5 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለስድስት ወር የሚመገብ በድርቅ ጊዜም የእንስሳ ምግብ ሆኖ የሚያገለግል በለስ /ካክተስ/ ከበለሱ ኬሚካል አመርታሎህ ብሎ ከሰሜን አሜሪካ የመጣ የውጭ ዜጋ በሙከራው ጊዜ ቫይረሱ አፈትልከ በመውጣትና ሰፊ ቦታ ብንፋስ ተሰራጭቶ እኖሆ ከራያ እስከ አፅቢ ወንበርታ ወረዳ፣ ሃገረሰላም/ተምቤን/ ደርሶ በለሱ አውድሞት ይገኛል፡፡ ወደ ዋናው የበለስ ማእከል የሆነው የአጋመም አውራጃ ተዳርሷል፡፡ ስለሆነም በለሱ በሙሉ ከወደመ በበለስ አብቃይ አከባቢ የሚኖሩ ህዝቦችና እንስሳት ትልቅ አደጋ ይደርሳል፡፡ እስካአሁን እንኳ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች በራያ፣ በዋጅራትና በእንድርታ ወረዳዎች ብዙ ሃብት ወድመዋል፡፡ ብዙ ህዝብና እንስሳ ለረሃብ ተጋልጧል፡፡ ወንጀል የፈፀሙ ተመራማሪዎች የጠየቃቸው ኃይል የለም፡፡ 76ሺ የዋጅራት ህዝብ በተወካዩቻው አማካኝነት አባይ ወልዱን ጠይቀው አድመኞች ተብለው ተባርረዋል፡፡ በለስ የአከባቢው ህዝብና እንስሳ ለምግብነት ብቻ ሳይሆን የሚጠቀሙበት እየለቀሙ ከትግራይ ፣ ጎንደር፣ ጎጃምና አዲስ አበባ ወስደው ሽጠው እጅግ ብዙ ገንዘብ የሚያገኙበት ሀብት ነበር፡፡

ብልሹ አሠራርና 40ኛው የህወሐት የልደት በዓል፡-

የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች እርሻ በመስኖ ክልሉ እንደለማና ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ደርሶ ወደ አግሮ እንዳስትሪ ለማሻጋገር እንዳስቻለ ይናገራሉ፡፡እዚህ ላይ አንድ ትልቁ ነገር የትግራይ ህዝብ በመስኖ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ጠቃሚ መሆኑ መረዳቱ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ሄደዋል፡፡ እዚህ ላይ መልካም ጅምር አለ፡፡ ወደ አገሮ እንድስትሪ ለመሸጋገር ደርሰናል የሚሉት ግን ውሸት ነው፡፡ በመስኖ ምርት ፋብሪካዎች ማቋቋም ይቅርና ለጊዚያዊ የምግብ ወጥም የሚሸፍን ቲማቲምና ሽንጉርት የለም፡፡ የትግራይ ህዝብ የሚጠቀም ከሱዳን፣ ከኦሮሞ፣ ከደሴ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ ህዝቦች፣ በተጨማሪም ከሱዳንና ከባህርዳር አከባቢ ነው፡፡በትግራይ መስኖ አለ የሚባለው ለጫቱ እርሻ ነው ፡፡

ለዚሁ ማስረጃ የሚሆነን ባለፈው አመት አራት ሃወርያት በትግራይ እየተባሉ የሚነገሩላቸው አቶ ስዮም መስፍን የሚመሩት አባይ ፀሃየ፣ ፀጋይ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ በትግራይ ክልል በመሬት ያለውን ሀቅ ለማጥናት ህዝቡ ጋ ወርደው ተመልክተው ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ የህወሐት አመራሮች የትግራይ ክልል መሪዎች የሚናገሩት የእድገት ሪፖርት ውሸት ነው በማለታቸው ትግራይ ውስጥ ከሚኖሩ የህ.ወ.ሃ.ት ማእከላይ ኮሚቴ ተጣልተው ዱላ የተማዘዙበት ወቅት ነበር፡፡

ህዝቡ በፍትህና በመልካም አስተዳደርም አልተጠቀመም፡ብለው 24 ዓመት ከድተውት የቆዩት ህዝብ በ11ኛው ሰዓታቸው ግን የጭንቀት ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ ምንም እንኳን የከዱት ቢሆኑም አሁን ያለው ሀቅ ግን ሊደብቁት አልቻሉም ፡፡ በተጨማሪም በጥቅምት ወር መጀመርያ የትግራይ ክልል መሪዎች ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ ባለስልጣኖችና በሃገር ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛ የህ.ወ.ሃ.ት ካድሬዎች ታማኝ አባለት ከ3000 በላይ የሚሆኑ በመቀሌ ሀወልት ሰማእታት ለ7ት ቀናት ተሰብስበው እነ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍንና ሰብሃት ነጋ ሲናገሩ የትግራይ ህዝብ ተስዋ እንጅ ለውጥ አለመጣንለትም ብለዋል ፡፡ስለዚህ የትግራይ ህዝብ 40ኛ ው የህወሐት የልደት ዓመት ሲያከብር ሀብታም ሆኖ ተለውጦ ሳይሆን በስደትና በረሀብ በአፈና ተማርሮ ለህ.ወ.ሃት መሪዎች እየረገመና ለለውጥ፣ ለዲሚክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለህግ የበላይነት፣ ለነፃነትና ለልማት ብለው ለተሰው፣ አካላቸው ለጎደለ ልጆቹ ለወደመ ንብረቱ እያስታወሰ ከንቱ መስዋእት እያለ የሚያከብረው በዓል ነው የሚሆነው ፡፡ ይህ ግን ስለጨነቀው ነው እንጂ የተከፈለ መስዋእት ትክክለኛ ዓላማ ነበር፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን ከድተውት ሁሉም ለሆዳቸውና ለክብራቸው ብቻ ሆነ ምን ያደርግ፡፡

40ኛው የህ.ወ.ሐ.ት የልደት በዓልና የመልካም አስተዳደር ዕጦት፡-
ህ.ወ.ሐ.ት ወደ ደፈጣ ውጊያ ሲዘምት 17 ዓመት ያህል በመቶ ሺ ሰዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከህዝብ አብራክ የወጡ የተሰውበት ንብረታቸው የወደመበት ከደርግ ፍፅም የተለየ ፍትህና ፀጥታ የሰፈነበት በመልካም አስተዳደር የረካ ህ/ሰብ ለመፍጠር ነበር፡፡ግን አልታደለም፡፡

በህ.ወ.ሃ.ት 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ሲያከብር ስንመከት ዜጎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በዳኝንነት፣ በህግ የበላይነት ማስጠበቅ ማለት በአሁኑ ግዜ የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ አይደለም፡፡በህዝብ ውስጥ አንድነትና ፍቅር እንዳይኖር በውስጣቸው የሰለላ መዋቅር አንድ ለአንድ ወጥመድ በመዘርጋት ከህ.ወ.ሐ.ት አስተሳሰብ ውጭ የማንም ሐሳብና እምነት እንደይኖር እያደረገ ይገኛል፡፡ የዳኞች ነፃነት የለም፡፡ ሌላው ቀርቶ በህግ ለተመረቁ ዳኞች ከህግ ውጭ የሆነ ለሁለት ዓመት በህ.ወ.ሃ.ት ፖለቲካዊ አመላካከት ፍርድ እንዲሰጡ ይሰልጥናሉ፡፡ ዳኞች የፈረዱት በፖሊስ ይፈረሳል፡፡ ፖሊሶች ፍርድቤት ሳይስታውቁት ዜጎች በህቡእ እስርቤት ማሰርና መግረፍ ወ.ዘ.ተ የተለመደ አሰራር ነው፡፡

በዚህ ክልል የፍትህ አካላት ለሰሙ ተቀመጡ እንጂ ወደዱም ጠሉም በህ.ወ.ሃት በረኸኛ አስተሳሰብ ነው የሚመሩ፡፡ በትግራይ በማናቸውም የመንግስት መስሪያቤት ጉዳይን ለማስፈፀም ጉቦ መስጠት በደላላ መስራት የተለመደ ነው፡፡ ያምሆኖ ጉዳዩ አይፈፀምም፡፡ ምክንያቱም በ`ላፍነቱ ያሉ የህ.ወ.ሃ.ት አባላት ስለሆኑ ሁሉ የሚሰሩት ማነው፡ ለማን የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ በትግራይ ያልታወጀ የቤት ውርስ ተደርÙል፡፡ ለዚሁ በማስረጃነት ለመጥቀስ የቤት አካራዮች ባለሃብቶች ከሚያከራዩት ሰው ተደራድረው የክራይ ተመን ተስማምተው በውልና ማሰረጃ ሄደው ይዋዋሉ የነበሩ፡፡ ይህ አሰራር ቀይረው ግለሰቡ ቤቱ ከማካራየቱ በፊት የገቢዎች ባለ ስልጣን ሰራተኞች ስንት እንደሚካራይ ቤቱንይተማናሉ፡፡ ለምሳሌ ቤት አካራዩ 2000.00 ብር ከተመነው እነሱ 5000.00 ብር ሊተሙኑት ይችላሉ፡፡ ወይም አካራዩ 1500.00 ብር ሲያከራይ አይሆንም 1000.00 ብር ነው የሚካራይ በማለት ይቀንሳሉ ወይም ይጨምራሉ ፡፡ ታድያ ይህ ቤት የማነው ፡ ደርግ በአዋጅ የግለሰዎች ቤት ወርሷል፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን ሳያውጁ የዜጎች ቤት እየሸጡ ነው፡፡ ይህ ተግባር በትግራይ ፍትህና መልካም አስተዳደር ያሳያልን ? አያሳይም፡፡

በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ 40ኛው የህወሐት ልደት ዓመት በዓል ሲያከብር እንዳይናገር በአፉ የተያዘበት በስለላ የታፈነበት፣ ሽብር በመፍጠር በማስፈራራት ገንዘብ ይዘርፋሉ፣ በወጥመድ ተጠፍሮ የተያዘበት እስከ ባልና ሚስት ገብተው የሰላይና ተሰላይ ሴራ በመፍጠር የአንድ ቤተሰብ አንዱ ሌላውን እንዲሰልል የተደረገበት ወቅት ደርሰናል፡፡ ስለዚህ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለ40ኛው የልደት በዓል ለማክበር የሚያወጡት ገንዘብ አቁመው የህብረተሰቡን ችግር በመፍታት ላይ ቢሰማሩ ለራሳቸውም ይበጃል፡፡አሁንም የብሄር ብሄረሰብ በዓል ይከበራል ባለፈውም የባንዴራ ቀን ተከብረዋል ብዙ ገንዘብ በክነዋል፡፡በህዝብ ጥቅም አንፃር ሲታይ ግን ዜሮ ነው፡፡

ሌላው የትግራይ ህዝብ በ17 ዓመት የትግል ዘመን አምባገነኑን ወታደራዊ ስርዓት አስወግዶ በዚሁ 40ኛ ዓመት ወታደራዊ አምባገነን ስርዓት አገርሽቶበት ሁሉም ነገር የሚሰራው በፖሊስ በድህንነት በካድሪዎች የበላይነት ነው የሚመራው ያለው፡፡ ይህ የሚያስቡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የመጨረሻዋ 11ኛ ሰዓት /ምፅኣት/ ዓለማቸው የደረሰች መሆኗ አይረዳቸውም፡፡

በ40ኛ በዓል ትግራይ በፀጥታና መረጋጋት ስንመለከታት የትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚ እድገቱ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደፊት መጥቋል እንደውም በትግራይ ያለው ልማትና በልፅግና ሞዴል ሆነዋል የሚባልለት ህዝብ በአሁኑ ጊዜ ሰራ-እጥነት፣ ስደት፣ መራብ፣ መታረዝ፣ ስላለ ወጣት ትውልድ ጥንቻውና ጭንቅላቱ እሚያሳርፍበት የስራ መስክ ባለመኖሩ በአሁኑ ጊዜ በከተሞች ስርቆት ማጅራት መች፣ የዜጎች ቤት ተከፍቶ መውረር፣ ህፃን አዛውንቱ በየጎደናው ይገደላል፡፣ አዛውንቶች ጥዋት ተነስተው ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የሚገደሉበት ሁኔታ አለ፡፡ መቀሌ በሞዴልነት ብንወስድ ዜጎች በየጎደናው ሙተው የሚገኙባት ከተማ ሆናለች ፡፡

በገጠርም እርስ በእርሱ ይገዳደላል፡፡ ፍትህ ያጡ ዜጐች ለወረዳና ቀበሌ መሪዎች የሚገድሉበት ህዝቡ ጭራሹን ሰግቶ የሚኖርበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የትግራይ እስር ቤቶች በእስረኞች ሞልተዋል፡፡ የታሰሩ ዜጎች እድሚያቸው ከ14 እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ያሉ አምራች ወጣቶች ናቸው፡፡
በትግራይ ክልል ህዝብ 17 ዓመት ለደርግ በደፈጣ ውጊያ ካሸነፈ በኋላ ሰላም፣ ፍትህ፣ ሰፍኖ እንዲኖር ይጠብቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ፍትህ፣ ነፃነት፣ የህግ የበላይነት ስላልተከበረለት ለዚሁ ሲል ስንት ሂወትና ንብረት ጠፍቶ አሁንም ህወሐት የጥፋቱን ጐደና ተከትሎ ሲሄድ ይታያል፡፡ ዋጋው ግን ሊከፍለው የማይችል ይሆናል፡፡

እቺ አገር ሰላም ናት እያሉ በአለም መድረክ እየወጡ የሚደሰኩሩባት በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ጠረፎች ከባድመ እስከ ሑመራ ከዛ አልፎም ወደ ክልል አማራ ጠረፎች ጋንቤላ የጥይት ጭሆት አልተለዮላቸውም፡፡ በአጠቃላይ በትግራይ በፍሽስታዊው ሻዕብያ ጎን ተሰልፎው ብዙ የደፈጣ ተዋጊዎች ተፈልፍለዋል፡፡

የደፈጣ ተዋጊዎች መፈልፈል ጠንቅ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ለትግራይ ህዝብ ከዘውዳዊው አገዛዝና ከፋሽስታዊው ደርግ የማይተናነስ አፈና እየፈፀሙበት ስላሉ ብቻ ነው፡፡
40ኛው የየካቲት 11 የልደት በዓልና ልማት፡-
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ወደ ስልጣን ኮሮቻ ከወጡ በኋላ በ24 ዓመታት ውስጥ ብዙ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ትምህርት ቤቶች ከመዋአለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዮንቨርስቲዎች ተገንብተዋል፡፡ ብዛት ያላቸው ተማሪዎች ተምረዋል፣ ብዙ መሰረተ ልማት እንደ መንገድ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብና ዝርጋታ፣ የውኃ አጠቃላይ ብዙ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ልማቶች ተሰርተዋል፣ በቕርቡ ደግሞ የግልገል ግቤ የአባይ ግድቦች፣ የባቡር ሃዲድ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ በከተማ ልማትም ብዙ ተሰርቷል፡፡
እነዚህ የልማት ስራዎች መኖራቸው ማንም ሰው የሚከደው አይደለም፡፡ ነገር ግን 1ኛ በ24 ዓመታት የተሰሩ የልማት ስራዎች በቂናቸው ወይ ሌላው ህ.ወ.ሃቶች እነዚህ ስራዎች የሰራቸው በትክክል ለህዝብ ጥቅም ወይስ ለስልጣን እድሜው ማራዘምያ ብሎ፡ በኔ እምነት እነዚህ የተሰሩ ስራዎች ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ተሰርተው ቢሆን ኖሮ ቅድሚያ ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ነበረባቸው፡፡ለህብረተሰቡ ከስራ እጥነት፣ከስደት አላዳኑትም፡፡ የተሰሩ ስራዎች ጥራት ያላቸውም፤ ዛሬ ተገንብተው ነገ የሚፈርሱ ናቸው፡፡ የሚሰሩ ፕሮዳክቶች በሙሱና የተጨማለቁ ናቸው፡፡ ስራው በሙያ በተካኑ ዜጎች ሳይሆን በካድሬዎችና በህወሐት ቀሳውስት በተደራጁ የልማት ብዱኖች በመሆኑ አመርቂ አይደሉም፡፡ በተለይ በትምህርት ጥራት እጅጉን የወረዳና ስራ ፈጣሪም አይደለም፡፡ ሁሉም ትምህር ቤቶች የህ.ወ.ሃት መሪዎችና አጃቢዎቹ የካድሬና የአባላት መመልመልያ በመሆናቸው ትውልድ ገዳይ ናቸው ፡፡

ስለሆነም በሃገራችን ያሉ መሰረተ ልማት የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሰርተናል ማን እንደኛ እያሉ የሚጎረኑበት ውጤታቸው የወረደና ለራሳቸው የስልጣን እድሜ ማራዘምያ ከፕሮጀክቶች በጀት ለራሳቸውና ለዘር መንዘራቸው፣ ለባንዳዎቻቸውና ጥቂት ጥገኛ ባለ ሃብቶች በሙሱና ለመመዝበር የተያያዘ ልማት ነው፡፡

ወራሪው ጣልያን ሃገራችንን በውጊያም ቢሆን ለ5 ዓመት ያህል ገዝቷል፡፡ በዚህ አምስት አመት የጭፍጨፋ አገዛዙ ለማራዘምና የባእድ ወረራው ለማስፋፋት የሃገራችን አንጥራ ሃብት ለመብዝበዝ ሲል በ5 ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ምንም የምድርና የአየር መገናኛ የስልክ ወዘተ ያልነበራት፣ ትምህርትም የማይታሰብ በነበረበት ወቅት 6000 ኪ.ሜ የመኪና መንገድ ሰርቷል፡፡ ብዙ ገጠሮች በወታደራዊ መንገድ ሊያገናኝ አድርጓል፡፡ ትምህርትም ከ1ኛ እስከ 4ኛ አልፎም እስከ 6ኛ ክፍል ከፍተዋል፡፡ ይህ የጣልያን ልማት ግን ለራሱ የባእድ ወረራ ስልጣን ከመጠናከር አልፎ ለኢትዮጵያ ያመጣው ጥቅም እጅጉን ትንሽ ነው፡፡ እንደ ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች 24 ዓመታት ቢቆይ ኖሮ ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማትና በእንዱስትሪ ከበለፀጉ አገሮች ተርታ ትቀመጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ደግሞ ህዝቡ በዚሁ የጣልያን የልማት ስራ አልረካም፡፡ ዋናው ጥያቄው ሃገራዊ ነፃነት ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ሊከበር ሉአላዊ ሃገር እንዲጠበቅ ወ.ዘ.ተ ስለነበር ጣልያንን አስወገዶ ልኡላዊ ሃገሩ ነፃ አደረገ፡፡

የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የመሰረት ልማት ግንባታና በየአመቱ በሁለት ድጅት የሚያድግ በየአመቱ 11% እድገት ያሳያል ቢሉንም ፍፁም ውሸትና በመሬት የሌለ ነው፡፡ የልማት እድገት ቢኖር ኖሮ ወጣት ዜጎቻችን በሃገራቸው እየሰሩ ጥሩ ማህበራዊ ኑሮ መስርተው በኖሩ ነበር፡፡ ነገር ግን የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የልማት እድገት መስፈርታቸው በራሳቸውና ዘርማንዘራቸው ምቾት በመሆኑ ባህር አቋርጦ ወደ አረብ ሃገር፣ አውሮፓና አሜሪካ ወደ አፍሪካ አገሮች ተበታትኖ የሚሰቃይ ያለው የተማረና ያልተማረ ወጣት እድሜና ፆታ ባማይለይ አይናቸውና አእሙራቸው አይመለከተውም፡፡ ስለሆነም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ዜጐቻችን ሆነው በ24 ዓመታት ሰርተውት ያሉ ስራ ከውጭ ወራሪው ጣልያን በ5 ዓመት ውስጥ የሰራው ሲነፃፀር እጅጉን ዝቅተኛ ነው፡፡ በሰብአዊ መብት አጠባበቅም ወራሪው ጣልያን ለአቦቶቻችን ጨፍጭፈው በትሩምብሊ አስሮ አሸብሮ ገድሏል የህዝብ ሃብት ወረዋል፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችም በ24 ዓመታት የአገዛዝ ዘመናቸው ብዙ ፖለቲኮኞች፣ ጋዜጠኞች ተማሪዎች ወጣት አርሶ አደሮች ገድለዋል፣ አስረዋል፣ ከአገር እንዲሰደዱ አድርገዋል፡፡ ስለሆነም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ከወራሪ ጣለያን የሚለያቸው ጣልያን የባእድ ዘር ነው፡፡ በተጨማሪም ቀለሙ ነጭ ነው፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ጥቁር ዜጐቻችን ናቸው በተግባር ከነሱ ጋር እኩል ናቸው፡፡ ጠቅላላ ባለመላኩ የህ.ወ.ሃ.ት የልማት ስራዎች በአሸዋ እንደ ተመሰረተ ቤት አይነት እንደሆነ በሃገራችን ችግር ያለፉቱ ህዝቦችን ከሰፍት ኔትና ከእርዳታ፣ ከስደት መብታተን ያላደኑ ሁሉም አይነት መብቶች የከላኩሉ ናቸው፡፡
በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች 40ኛው የልደት አመታቸው ውጤታቸው ይህ አልነበረም፡፡ ተራማጅ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አምጾኞች ከያኒያን፣ ፀሃፊዎችና አስታማሪዎች በምንሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ወደ ደፈጣ ውጊያ ሊዘምቱ ካደረጋቸው አንዱ የነፃ ፕሬስ ዕጦት፣ የመፃፍ የመናገር ዕጦት፡፡ የመድብለ ፓርቲ ነፃነት ዕጦት ወ.ዘ.ተ ጥያቄዎቻው ለመመለስ ነበር፡፡ ለነዚሁ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ብዙ ኢትዮጵውያን መስዋእቲ ከፊለው በታለ፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችም ለይስሙላ የእንታይ እንታይ ባህሪያቸውና የአለም ህብረተሰብ ለማታለል በመጀመሪያ ብዙ ነፃ ፕሬሶች ተፈጠሩ፣ ብዙ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተፈለፈሉ፣ ብዙ የተለያዩ ሃሳቦች ፈለቁ፣ ህዝቡ ተስፋ ጥሎ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የህዝብ ፍላጎት አጨለሙት፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን ፀረ ዲሞክራሲ የሆነ ባህሪያቸው ተደብቆ ሰለማይደብቅ በህገ-መንግስት ሰፈሮ በነጋሪት ጋዜጣ የታወጁት መብቶቸ ቀስ በቀስ እየ ሽረሽራዎቸው መጣ፡፡ ፕሬሶቹም ቀስ በቀስ እንዲዘጉ ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ አደረገ፡፡ ቆይቶም በወቅቱ ሰላማዊ ሁኔታ ተገኘ ብለው ብዙ ፓርቲዎች ተመሰረቱ፤ እነሱም ቀስ በቀስ ሆነ ተብሎ ወደ ደፈጣ ውጊያ እንዲዘምቱና እንዲመቱ ተደረገ፡፡ ብዙ የደፈጣ ተዋጊዎች ተፈጠሩ፡፡ ጥቂት ጋዜጠኞች አሳታሚዎች ቀሩ፡፡ እነሱም በ1997 ዓ.ም የፓርላማ ውድድር ታሰሩ ካገር ተሰደዱ የተገደሉም ነበሩ፡፡
ከዛ በኃላ ሁኔታው እየጠበበ መጣ የፓርላማ ምርጫም አጨለሙት፡፡ በሰላም ለሚታገሉ ፓርቲዎችም መሪዎቻቸው በተለይ ወጣት አመራሮች ተወዳድረው በስተጀርባቸው ብዙ ህብረተሰብ ያሳልፋሉ ለሚሉዋቸው እየመረጡ ቃሊቲ ቅንሊቶ አገቡዋቸው፡፡ ጋዜጠኞችና አስታማሚዎች አብዛኞቹ ሆን ብለው ሽብር እየፈጠሩ ወደ ውጭ እንዲሰደዱ ተደረጉ፡፡ እጅግ ብዙ ጋዜጠኞች፣ አስታማሚዎችና የድህረ ገፅ ፀሃፊዎች ታሰሩ፡፡ ጋዜጣ አዘሪዎች በተለይ በትግራይ እንደይሸጡ ተከላከሉ፡፡ ብዙ ጋዜጦች ተዘጉ፡፡ ተቃናቃኝ ፓርቲዎች ስብሰባ እንዳይቀመጡ፣ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ ተከላከሉ፡፡በራሪ ወረቀት ለመሰራጨትም ተከላከሉ በሄዱበት ይታሰሩ አሉ፡፡ አሁን ደግሞ የፓርቲ አባላትና አማራሮች አሸባሪ ሰላዮች እየተባሉ ከከልሉ እየተለቀሙ አዲስ አበባ ከህ.ወ.ሃ.ት የድህንነት ምርመራ ክፍል ታጉረዋል፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት የድህንነት ምርመራ ክፍል ታጉረዋል፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች 40ኛው የልደት በአላቸው ሲያከብሩ እነሱ ሲፈንጠዙ፤ የትግራይ ህዝብ ደግሞ በአፈናና ጨለማ ተውጠዋል፡፡የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ውጤት፣የየካቲት 11 ውጤት ይህ ሆኖ ቀረ፡፡
በ40ኛ የህ.ወ.ሃ.ት የልደት በዓል አጥቢያ የሚካየደው የፓርላማ ውድድር ካለፉት ፀረ-ዴሞክራሲ ምርጫዎች በጨለመ መንገድ ለማካየድ ተዘጋጅቷል፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ በተመሰረተ ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም ብለው መሆን ሲሳናቸው በደፈጣ ውጊያ ስርዓቱን ለመቀየር በረሀ ገቡ፡፡ህወሐት ከ40 ዓመታት በፊት ይቃወመው ለነበረው ስርዓት መልሶ ሲተክል ይታያል፡፡የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በአገሪቱ ከአንድ ፓርቲ በላይ አያስፈልግም የሚል መርህ በመከተል በኢትዮጵያም ወደ ፓርላማ አንድ ሰውም ይሁን ተቀናቃኝ ፓርቲ አባል አያስፈልግም በማለት የ2007 የፓርላማ ምርጫ አጨልምውቷል፡፡ይህ ነው የ40ኛ የህ.ወ.ሃ.ት የልደት በአል ፡፡የየካቲት 11 ውጤት፡፡
40ኛው የልደት በአላቸው ደግሞ በሞቶ ሺ የሚቆጠር እንደምተኛ በመሰብሰብ የኢትዮጵያ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ ታማኝ ልናደርገው ነው እያሉ ከወዲሁ ይቀሰቅሳሉ፡፡ ተቋዋሚዎች ግን ሁሉ አይነት ቅስቀሳ እንዳያደርጉ ታግደዋል፡፡ የሚድያ ሽፋን የሚባል አይታሰብም፡፡ ዘመናዊ ፋሺዝም በኢትዮጵያ አገረሽቶ ይገኛል፡፡ በተለይ ደግሞ በክልሎች የባሰ ስለሆነ 40ኛ የህ.ወ.ሃ.ት ልደት በአል የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ፈንጠዝያ የሚበረታበት ዜጐች በስደት በወህኒ ቤት በረሃብ በአፋና የሚሳቃዩበት ነው በዓሉ፡፡
የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎችና ኢፈርት በ40ኛው በየካቲት 11 የልደት በዓል፡-
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች፣ አጃቢዎቻቸውና አጋር ፓርቲዎች በ40ኛው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የልደት በአል ሲያከብሩ በህዝቦች መስዋእት የፀደቀው ህገ መንግስት በመናድ በኢ/ያ የሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል የሚያራምዱ ፓርቲዎች የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ፓርቲ ጭምር መፈፀም ያለባቸው በህገ መንግስት የተደነገገው ማናቸውም ፖለቲካዊ ፓርቲ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ የንግድ ስራ ሊሰራ አይፈቅድም ይላል፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን በህዝብ ትግል የፀደቀው ህገ መንግስትና ድንጋጌ ወደ ጎን በመጣል እነዚህ ህግ የማይገዛቸው አምባገነን ፓርቲዎች እጅግ ብዙ ቢልዮን የሚገመት ካፒታል ያላቸው እንድስትሪዎችና የችርቻሮ ንግድ እያንቀሳቀሱ የኢንፖርትና የኤክፖርት ንግድ በመቆጣጠር እንዱሁም በትራንስፖርት፣ በኮንስትራክሽንና በእንድስትሪ በማስማራት ግለሰዎች ሊሰሩት የሚችሉ ስራዎች ጨምድደው በመያዝ በተጨማሪ በሑመራ፣ በመተማ፣ በራያና ቆቦ የሚገኜው በመቶ የሚቆጠር ሄክታር ከህዝብ በመቀማት ራሳቸውና ጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ባለሃብቶች ሆነው ጠያቂ የሌላቸው ምዝበራ ያካያዳሉ፡ ህዝብም የፍትህ ያለህ ብሎ ጭሆ ሰሚ ጀሮ አጥቷል፡፡

እነዚህ የተዘረዘሩት እንድስትሪዎችና የንግድ ማእከላት የአመት ትርፋቸው በብዙ ቢልዮን የሚገመት ሲሆን የውስጥና የውጭ ሂሳብ ሸም(ኦዲት) የማይደረጉ ናቸው፡፡ ይህ ሃብት በጥቂት የህ.ወ.ሃ.ት ፖሊት ቢሮ (ስራ አስፈፃሚ አባላት) ወደ ፈለጉት የሚያንቀሳቅሱት ሀብት ነው፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ የማን ነው ተብሎ ሲጠየቅ አንድ ግዜ የአካል ጉዳተኞች፣ ሌላ ግዜም የህዝብ ናቸው ይላሉ፡፡ የትግራይ ህዝብ ግን በየአመቱ በቢልዮን ከሚገመት ትርፍ አንድ ሳንቲምም ቀምሶ አያውቅም ፡፡ ለማታለል ያህል ግን በቅርብ ግዜ ለተነሳላቸው ጥያቄ ለማብርድ ከ300 ሚልዮን ብር ብቻ የሚገመት ጥቂት ት/ት ቤት አሰርተዋል ሊያሰሩ ናቸው፡፡
በዘንድሮ በ2006 ዓ.ም ከ28 የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች እንዳስትሪና የንግድ ማእኸላት ውስጥ ከስሚንቶ ፋብሪካ፡ከሱር ኮንስትራክሽን ከትራንስ ኢ/ያ ፡ከመስፍን እንጀነሪንግ ብቻ ከ4 ቢልዮን በላይ የተጣራ ትርፍ አግኝተዋል፡፡ታድያ የ24 ዓመታት የድርጅቶች በዘንድሮ ያለፉት አመታት ትርፍ የት አለ ፡ ይህ ጥያቄ በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች መልስ አይገኝለትም፡፡ አንድ አሰዛኝ ነገር ግን የትግራይ ህዝብ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ ፡ በስብኣዊና በዲሚክራሲ መብቶች፣ በልማት፣ በማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነቱ ከሁሉም ክልሎች ጅራት እያለ የሌላ ክልል ህዝቦች ወንድማቸው የትግራይ ህዝበ ምንም ተጠቃሚ ያልሆነ የህ.ወ.ሃ.ት በየትልልቅ ከተሞች የሚገኝ ዘርመንዘራቸው ሃብት እየተመለከተ የትግራይ ህዝብ በባዶ ሆዱ አደገ፡ ተመነደገ፣ በላ፣ ጣጣ፣ ትግራይ የኢ/ያ ሃብት ወራ በእድገት ሰጠመች ይላሉ፡፡

የትግራይ ህዝብ ግን ፆታና እድሜ በማይለይ በስደት እንደለ ተደጋግሞ ተገለፀዋል ፡፡ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን አብዛኛው ህዝብ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ፣ በቂ ህክምና አላገኘም፣ በኔትወርክ፣ ኤሌክትሪክም አጠቃቀም እጅጉን ተሰቃቀይቷል፡፡ እንግዲ 40ኛ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በአል ውጤt$ ይህ ነው፡፡
አንድ ሃቅ ግን አለ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በሞኖፖል የያዙት የህዝብ ሃብት እንዳይታወቅ በውጭ ያሰፈሩት ገንዘብ ለመሸፈን የልጃቻቸውና ዘርመንዝራ ቸው ምቸትና መቀማ-ል እንዳይታወቅ ለመሸፈን በትግራይ አንድ ግድብ½ Xንድ ብርቱካናና ፖፖዮ በአንድ መንደር የምትታይ እርሻ ወይም ለህዝብ ለውጥ እንኳ ቲማቲም በበቂ ይዞታ የማያቀርብ መሰኖ አስር ግዜ በልማታዊ የውሸት ጋዜጠኛ እየሳሉ ለማኸል ሃገር አደናግሮውታል ፡፡ ይህ የማኸል ሃገር የህዝቡ መደናገር አሁንም አልተቀረፈም ፡፡ በትግራይ ያለው ችግር መጥታችሁ ብታዩ ደስታው አልችለውም፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኛ ውሸት እንኳ የኢ/ያ ህዝብ ያውቃዋል፡፡
የህ.ወ.ሃት መሪዎች ግን ለ40ኛው የልደት በኣላቸው ለህዝብ መደናገርያ በሰላም የታጀበ ድራማ ከወዲሁ እያዘጋጁ ናቸው፡፡እኔ የሚያሳዝነኝ ግን በኢ/ያ ያሉ በተለይ በትግራይ ያሉ ጋዜጠኞች በመሬት የሌለ የውሸት ዘገባ እየዘገቡ ህዝብ የሚያዳናግሩ ልማታዊ ጋዜጠኞች ተብለው የሚጠሩ ወጣቶች በህፃንነታቸው በውሸት መካናቸው ይገርመኛል፡፡

የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የሰበሰቡት ሃብት የኢፈርት ብቻ አይደለም፡ በትግራይ በሰመ አካል ጉዳቶኞች 24 አመታት ሙሉ ከኢ/ያ ህዝብና ከውጭ እርዳታ ሰጪ ተለምኖ የመጣ ገንዘብ የተÌÌሙ የአካል ጉዳተኞች ሃብት የሚባሉ ካፒታላቸው በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ትላልቅ ህንፃዎች የትራንስፖርት ኩባንያ ፡ሌሎች የንግድ ድርጅቶች አሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የሚመሩት በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ናቸው፡፡
እነዚህም የሚቆጣጠራቸው የለም፡፡ በትግራይ ከላይ እንደጠቀሰኩት 126ሺ አካል ጉዳተኞች አሉ፡፡ ይህ አሃዝ ሊጨምር እንጅ የሚቀንስ አይደለም፡፡ እነዚህ ከ4500 እስከ 6000 ጉዳተኞች ብቻ የቦርድ (ጡሮታ አበል ያገኛሉ ፡፡ ሌሎች ጡሮታና አበል ያላቸው ህክምና እርዳታ አያገኙም፡፡ ሌላው በትግራይ የትግራይ እርዳታ ማህበር (ሬስት) የሚባል እጅግ ግዙፍ የዶላር ምንጭ የሆነ ድርጅት አለ፡፡ ይህም በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቁጥጥርና አማራር ነው፡፡ በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቅንነት ካላችሁ የ40ኛ አመት ስታከብሩ ሁለት አስተያየቶች ልስጣችሁ፡፡
ለ40ኛው አመት የምታወጡት ግዙፍ ባጀት፣
የኢፈርት የሬስት ገንዘብ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ሃብት ላገር ውስጥና በስደት ያለው ወጣት እንዲÌÌመበት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በመቅረፅ ስራ መፍጠር እነደዚሁም በከተማ ያለው ስራ አጥ የተማረ ሃይል ሰውም የተማረው ሞያው ሳይረጅ (ሳይደነዝዝ) ስራ ፍጠሩለት፡፡ ይህ አስተያየት ካልመለሳችሁ የተቸገረና የተራበ ህዝብ ምን ሊያደርግ እንደሚችል በሚገባ ታዉቁት አላችሁ፡፡

አንዳንድ ወገኖች ህ.ወ.ሐ.ት ከማለት ፈንታ የህወሐት መሪዎች ብለህ መጻፍ ይቀነሃል ለምን የሚሉ አሉ፡-
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች እያልኩኝ የምፅፈው በኔ እምነት ህ.ወ.ሃ.ት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ማለት ህዝባዊ አመፅ ማለት ነው፡፡ አንዳ አንድ ወገኖች ወያነ እያሉ ይጠራሉ ፡ እንደ ስድብም የሚቁጡሩት አሉ፡፡ ይህ አላማወቃቸው ነው እንጂ ወያነ ማለት በበረኸኛ አነጋገር ለለውጥ የሚያምፅ ህዝብ ማለት ነው፡፡ ህ.ወ.ሃ.ትም ከዛ የወረሰው ህዝባዊ መያነ ብሎታል ፡፡ ይህ ማለት ዳግም ለለውጥ የተነሳ ህዝብ ማለት ነው፡፡ የትግራይ ወያነ ለምን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ተባለ እርግጥ ህ.ወ.ሃ.ት በጥቂት ተጀምሮ እያደገ እያደገ የመጣ ነው፡፡ በመጀመርያ ህዝባዊ ወያነ አልበነረም፡፡ የኋላ ኋላ ግን ደርግ ሞኝ ነበርና ተ.ሓ.ሕትና ህዝብ ሳይላይ በከተማም በገጠርም የነበረ ህዝብ በጃምላ በጣላትነት ፈርጆ በመጨፍጨፍ ሁሉ የትግራይ ህዝብ አምፀዋል(ወያነ) በመሆኑ ወያነ ማለት የትግራይ ህዝብ ማመፅ የሚገልፅ ነው ፡፡
ወያነ ማለት ደግሞ ለትግራይ ህዝብ የተሰጠ ስም ብቻ አይደለም ፡፡ በኢ/ያ ከህ.ወ.ሃ.ት በፊት የኦሮሞ፣ የሶማል፣ የደብረታቦት፣ የትግራይ ተማሪዎች አመፅ /ወያነ ነበር ምክንያቱ ህዝቡ ለለውጥ ወይነዋልና፡፡ አሁን ያለው ለውጥ ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የሚቃወም ህዝባዊ አመፅ ከተነሳ እንደ 1997 ዓ.ም ምርጫ ያለ ማእበል ወያነ ሊባል ይችላል ፡፡ ይህ ስም በሰልጣን ላሉ አምባገነኖች የሚሰጥ አይደለም፡፡

አሁን የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ወያኔዎች ናቸው ወይ ፡ በኔ እምነት የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በዘለማድ ነው እንጂ ወያነ አይደሉም ወያነ የሚል ስም በ1983 ዓ.ም ግንቦት 20 አብቅቷል ፡፡ ምክንያቱም ፀረ-ደርግ አመፅ መቋጫ አግኝቷል፡፡ ስም መቀየር ነበረበት፡፡ አሁን በባሰ ዲክታቶርያል ስርአት ሆነዋል፡፡ ጨቋኝና አፋኝ ነው፡፡ በመሆኑም ወያነ የሚል ስም ፀረ ዲክታቶሮች ለሚታገሉ የህዝብ አመፅ ነው መሰጠት ያለበት፡፡

በመሆኑ አንዳ አንድ ወገኖች ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሲቃወሙ ወያኔዎች እያሉ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ህዝብ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ህዝባዊ አመፅ (የህዝብ )ወያነ ድል እንዲቀዳጅ ላደረጉት የህዝብ ታጋዮች በሙሉ እንደስድብ የሚጠቀሙበት ቃል ሆነዋል ፡፡ ይህ ስድብ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የኸው ወያኔ እያሉ ይሰድቡሃል በማለት የራሳቸው ትርጉም ይሰጡታል ፡፡ ስለዚህ ወያነ የሚል ስም ለለውጥ ለሚያምፅ የሚሰጥ ስም እንጅ ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች አይመለከትም ለነሱ የሚመለከት የነበረ ከ1983 ዓ.ም ግንቦት 20 ነበር ይህ በወቅቱ መቋጨ አግኝታል ፡፡ ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ወያነ ብሎ መጥራት ሽልማት እንደ መስጠት ስለሆነ መታረም አለበት፡፡
ማጠቃላይ
በዚህ ፅሁፍ ስለ የህ.ወ.ሃ.ት 40ኛ የትጥቅ ፍትግል የልደት በአልና ክሱ የተያያዙ ችግሮች ለመፃፍ የተገደዱኩበት የየካቲት በአል ሊከበር ጥቂት ቀናት በወሩበት በአሁኑ ግዜ በሃገራችን የህዝባችን የከፋ ድህነት የንሮ ውድነት እያሉ ስራ አጥነት ተሰፍፍቶ በችግር ምክንያት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የኢ/ያ ወጣቶች ተቸግረው በ360 ዲግሪ የኢ/ያ ጠረፎች ዘለቀው እየፈለሱ እስከ ባህር ማዶ ሊሻገሩ የአስቀለብና ኩላሊታቸው እየተቆረጡ የት ጃሮች የኩላሊትና የሌላ ስፔርፓርት እየሆኑ ሳሉ በሄዱበትበት አገሮች እንደፍጡራን የማይቆጠርበት በፎቅ እየተጣሉ አስቃቂ እርምጃ እየተወሰደባቸው ሲሰቃዩ፤ ለነዚህ ዜጎች የሃገራችን ገንዘብ በቁጠባ በመያዝ እንዲÌÌሙ ከማድረግ ፋንታ ለአንድ ፓርቲ በአል በየአሉበት ታስባል ብሎ ከማሳለፍ ይልቅ በመቶ ሽዎች ለሚቆጠሩ ስራአጢ ወገኖች ማቋቋም የሚሆን እጅግ ብዙ ሚልዮን ብርና በብዙ ሚልዮን የሚፈጅ ቁሳቁስ ማባከኑ አስገራሚም ወንጀልም ከመሆኑ ሌላ ለፓርቲዎችም መጥፎ ትምህርት ስለሆነ ከወዲሁ በአጠቃላይ የኢ/ያ ህዝብ በተለይ በቅርብ የበይ ተመልካች የሆንክ የትግራይ ህዝብ ይህን ብክነት በመኮነን ጠንክሮ ተቃውመህን ማሰማት ይጠበቅበሃል ፡፡ ቤት ዘገተህ የስለላ መዋቅር ሰግተህ ማማት ፋይደ የለውም፡፡
በሌላ በኩል ክልሎችና ግለሰዎችም መጥፉ ተመክሮ ስለሆኑ መላው የኢ/ያ ህዝብ ተቃውሞ አቅርቦ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና አጃቢዎቹ አመት ሙሉ የፓርቲዎች የልደት በአል የባንዴራ ቀን፣ የብሄር ብሄረሰቦች ወ.ዘ.ተ ይደረጋሉ ፡ በበኩሌ ባንዴራ፣ የብሄረሰብ በዓል ታስቦ መዋል አልቃወምም ፡ እኔ የምቃወመውና ህዝብም መኮነን ያለበት በየአመቱ የሁሉም በአላት በቢልዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ መባከን ወንጀል ከመሆኑም በላይ ህግ ቢኖር ያስቀጣልም ፡፡በመሆኑም ሙሁራን፣ ተማሪዎችና የስደት ሰለባ የሆናችሁ ወጣቶች ለአባከኞቹ ተቃውሞዋችሁ አሰሙ፡፡
የዚህ ፅሁፍ አርእስት የትግራይ ህዝብ ባለፉት 24 አመታት እስከ የህ.ወ.ሃ.ት 40ኛ የልደት በአል ለካቲት 11 ምን ተጠቀመ ለሚለው በሰፊ ለመግለፅ ምክሬአለሁ ፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ የኢ/ያ ህዝብ በተለይ የትግራይ ህዝብ ያገኘው ጥቅም በሁሉም መሰክ ውሃ ቢወግጡት እምቡጭ ነው የሆነው፡፡ በዚሁ ዘመን ደልቶዋቸው የሚገኙ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና አጃቢዎቻቸው እንዲሁም ከነሱ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ባለሃብቶች ናቸው፡፡ሌላው ህዝብ ብሩህ ተስፋ የማይታየው በጨለማ ተውጧል፡፡የትግራይ ህዝብ 40ኛ አመት የልደት በአል ሲያከበር ተጠቋማል በልፀጓል የሚል ካለ መጥቶ ይመለከት፡፡
ማሳሰብያ ለህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ኣጃቢዎች
በአሁኑ ግዜ ትግራይ የአካል ጉዳተኞች የተሰው ታጋዮች ወላጆችና ሌሎች አረጋውያን መንደር ከመሆኗ በሻገር ምክንያት እናቶችና ህፃናት በሁለቱ ጠርነት አባት እናት ያጡ የሚያስተሙራቸው ወገን ያጡ፣የኤች.አይ.ቪ ህመምተኞችና በዚህ በሽታ አባት እናት ላጡ ህፃናት፣ አንስተኛ የጡረታ አበል ለሚያገኙ አረጋውያን በተጨማሪ ለስራጥ ወጣቶች ብታቋቀቁሙበት ከዚህ አልፍችሁ እኔ ከመትኩ ሰርዶ አይብቀል የምትሉ ከሆነ ህዝብ ሃያል ነውና አንድ ቀን ይፋረዳቹኋል፡፡
ደርግ ፋሽስትና ጨካኝ ነበር አንድ ቃል ኪዳን ግን ነበረው በጦር ሜዳ ለሞቱት ወታደሮጅ የወታደር ልጅ እንክብካቤ ማግኘት አለበት ከሚል እምነት ህፃናቶች በመሳባሰብ ባጋር ውስጥ በራሽያ ፡ በዙንባቤ እየላክ አስተሙሩዋቸዋል፡፡ ብዙዎች በአሁኑ ግዜ ላገራቸው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡፡ ጃንሆይም ለወታደር ልጆች የባለውለታ ወገን ነው ፡ በማለት ግዙፍ እርዳታ ያደርጉ ነበር፡፡ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ግን ለዚህች አገር በቅንነት ላገለገሉ እንክብካቤ ከማድረግ ፈንታ ተጠቀመው ይጡሉታል እንጅ ባለውለታቸው አያውቁም፡፡
ከአስገደ ገ/ሥላሴ መቀሌ

ይቀጥላል