የዘጠኝ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫዉን ያለ ቅድመሁኔታ ለመሳተፍ መወሰናቸው የሚገልጹ ዘገባዎች እየወጡ ነው ‪

Image
በቅርቡ የአንድ ወር መርሃ ግብር አዉጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲና የዘጠኝ ድርጅቶች ስብስብ፣ ፓርቲዎች ትብብር፣ ያለ ቅድሜ ሁኔታ በመጪው የ2007 ምርጫ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን የምገልጹ አንዳንድ ዘገባዎች በተለይም በዳያስፖራ አካባቢ የሚሰሙ እንደሆነ ቢታወቅም፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ በፌስ ቡክ በግልጽ በሰጡት አስተያየት፣ ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ አለማስቀመጡን ገልጸዋል።

“NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir that is under action by its members and Blue is not an exception to present and decisions are being made in participatory process.” ሲሉ የትብብሩ አባል ድርጅቶች ለምርጫ የሚያስፈልገውን የምርጫ ምልክት በአስቸኳይ ለመዉሰድ መስማማታቸውንም አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል።

በዚሁም መሰረት፣ የሰማያዊ ፓርቲንም ጨምሮ ሌሎች የትብብሩ አባል ድርጅቶች የምርጫ ምልክት ከሌሎች ድርጅቶች ቀድመው እንደወሰዱም የሚገልጹ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ምርጫ ቦርድ ከአንድ ሳምንት በኋላ የድርጅቶቹን ምልክት ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ የሰማያዊን ጨመሮ የሌሎች ድርጅቶች የምርጫ ምልክትም ምን እንደሆነ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ የትብብሩን ዉሳኔ አስፈላጊና ጠቃሚ ዉሳኔ ሲሉት፣ ሰማያዊ/ትብብሩ ወደ ምርጫ ያለ አንዳች ቅድሜ ሁኔታ ለመሳተፍ በመወሰኑም፣ በምርጫው ረገድ ከአንድነት ፓርቲ ተመሳሳይ አቋም እንደያዘ በግልጽ ያመላከት እንደሆነም አስረድተዋል።

“ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ ለመግባት ሰማያዊ/ትብብር ከወሰኑ፣ ለምርጫው መዘጋጀት አለባቸው። ድርጅታዊ ሥራ ላይ ማተኮሩ የድግ ነው። ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸው ከነ አንድነት ጋር በምርጫው ረገድ መተባበር ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ እኙ ተንታኝ ትብብሩ ወደ ምርጫ ከገባ ዘንዳ የምርጫ ዘመቻውን አብሮ ከሌሎች ጋር ለማቀናጀት እንዲዘጋጅም ጠይቀዋል።

በተያይዘ ዜና የአንድነት ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች በማስመረጥ ዙሪያ በተቻለ መጠን ገለልተኛ የሆኑ የሕዝብ ታዛቢዎች እንዲመረጡ ለማድረግ በየዞኖቹና በየወረዳዎች ስምሪት እንደጀመረም ለማወቅ ችለናል።

አቡጊዳ