በኢሕአዴግ ድርጅቶች መካከል የውስጥ ፍጥጫው አይሏል።

ኦሕዴድ ከኢህአዴግ ተለይቶ ራሱን የቻለ ፓርቲ እንዲሆን የሚፈልግ ቡድን ተነስቷል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በዚህ በያዝነው ነሃሴ ወር ውስጥ ብቻ የሕወሓት/ብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እና አንጋፋ ታጋዮች የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን ባገለል እና ባላሳተፈ በተከታታይ የተደረጉ ተደራራቢ ስብሰባዎች በኦሕዴድ አመራሮች ዘንድ ጥያቄን ያጫረ ሲሆን በደሕዴግ አመራርች ዘድ ደሞ የዝምታ ድባብ እንዲያጠላ በማድረጉ በኢሕአዴግ ድርጅቶች መካከል በአዲስ መልኩ የውስጥ ፍጥጫ ማየሉን የድርጅቱ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የኦሕዴድ አመራሮች በኢሕአዴግ ውስጥ የሚደረጉ ስብሰባዎች ለምንድነው የድርጅታችንን ሰዎች የሚያገሉት የሚሉ ጥያቄዎች ስእሞኑን ለሙክታር ከድር እና ለአባዱላ ገመዳ የቀረቡ ሲሆን እስከመቼ በሕዝብ ተተፍተን በሃይል ብቻ ለመኖር እንችላለን ኦሕዴድ ከኢህአዴግ ተለይቶ ራሱን የቻለ ፓርቲ በመሆን ተሃድሶ እንዲያደርግ ካልሆነ ድርጅቱ ከአንድ አካል የበላይነት የሚላቀቅበት መፍትሄ እንዲፈለግ ሲሉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በዚህ ወር ወስጥ ኢሕአዴግን ለማዳን በሚል የተለያዩ ስብሰባዎች በቀድሞ አንጋፋ ታጋዮች በሆኑት እና በሲቪል እና ውታደራዊ ስልጣን ላይ ባሉት የሕወሓት እና የብአዴን አመራሮች ተከታታይ ስብሰባዎች እየተደረጉ ሲሆ የወያኔው ጁንታ ዜጎች እየሰበሰበ በማሰር እና በሕዝቡ ዘንድ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንድሁም ስም በማጥፋትና በተለያዩ እኩይ ተግባሮቹ በውጪም በውስጥም በደረሰበት የፖለቲካ ኪሳራ ለመጪው አመታት ሕዝቡን እንዴት አታሎ እና አጭበርብሮ መግዛት እንዳለበት እቅድ እያወጣ ሲሆን ለአዲስ አመት መጀመሪያም የኢሕአዴግ አመራሮችን ሰብስቦ መመሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ወያኔ ሲፍረከረክ አጋጣሚዎችን መጠቀም እስካሁን ያልቻሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁንም በወያኔ ላይ የደረሰውን ኪሳራ ትጠቅመው አፋጣኝ የፖለቲካ ድሎችን በማስመዝገብ የበሰበሰውን ስርአት ወደ መቃብር እንዲወርድ ያላሰለስ ትግል ማድረግ አለባቸው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራል።