በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ወላይታ ሶዶ 18 ሰዎች ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨለማ ቤት ታስረዋል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ!
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ወላይታ ሶዶ 18 ሰዎች ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨለማ ቤት ታስረዋል::
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!" የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ማስፈራሪያ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች
ምንሊክ ሳልሳዊ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ሃይለማርያም ደሳለኝ ምንጭ ናት በምትባለው በወላይታ ሶዶ ከከፍተኛ ደረጃ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች አጋለጡ::ነዋሪዎቹ እንዳሉት ካለምንም ምክንያት የሚያፍኑ የሚያስሩ የሚገርፉ እና ከፍትህ እና ፍርድ ቤት በላይ የሆኑ ትናንሽ ቡድናዊ መንግስታት እና እንዳሻቸው በህዝቡ ላይ የሚፈነጩ ካድሬዎች የወላይታን ህዝብ በስቃይ እና በሰቆቃ ውስጥ እያኖሩት መሆኑን ነዋሪዎቹ አማረው ተናግረዋል::
ባለፈው ሳምንታት ውስጥ እንኳን ከተያዙት የወላይታ ነዋሪዎች መካከል አቶ አየለ ሃሚሶ የሚባል የከተማውን የፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት እና ዳኛ ደብድባችኋል ተብለው ካለምንም ማስረጃ 18 ሰዎች ተይዘው ላለፉት አስረ አምስት ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በጨለማ ቤት ታስረው ይገኛሉ::እነዚህ እስረኞች የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሌሊሼ ኦላ እና ግብረበሮቹ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን እንዲሁም ደብዳቢዎቹን ጭናችሁ አድርስቹሃል የተባሉ የባጃጅ ሹፌሮች በቁጥጥር ስር ውለው እየተገረፉ መሆኑን በስቃይ ላይ ያሉት እስረኞች ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በሽብርተኛነት እና ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዛቹሃል በማለት እንግልት እና መንግስታዊ ሽብር በከተማው የፖሊስ አዛዥ እና ግብረአበሮቻቸው የተፈጸመባቸው ሲሆን በሻንጣዎቻቸው ላይ ፍተሻ አድርገው ምንም የጦር መሳሪያ እንዳላገኙ እና "ወላይታ ለመግባት ምንም አይነት ፈቃድ ከማንም አንጠብቅም ምክንያቱም አገራችን ነው" በማለት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ቢመልሱም "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!" የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ
አድርሰውባቸዋል::
ዛሬ የካቲት 26 2006 "አሁን መሄድ ትችላላችሁ" ብለው ከአዲስ አበባ የሄዱትን ሶስቱን የሰማዊ ፓረቲ አመራሮች 1ኛ/ አቶ ጌታነህ ባልቻ 2ኛ/ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 3ኛ/ አቶ ይሁን አለሙ ሲለቁዋቸው ከሀዲያ ጀምረው የሰሯቸውን ስራዎች የያዙበትን ሰነዶች፤ቃለ ጉባኤዎች እና ሁለቱን የወላይታ ተወካዮችን /አስተባባሪዎችን/ እስካሁን ያለቀቋቸው ሲሆን ስለ ንበረታችሁ የምናውቀው ነገር የለም በማለታቸው ንብረቶቻቸውን ሳይረከቡ ወደ አርባምንጭ መንቀሳቀሳቸው ታውቋል::
የታሰሩት የሰማያዊ ፓረቲ የወላይታ አስተባሪዎች ባይፈቱም፤ የተወሰዱባቸው ንብረቶች ባይመለሱላቸወም ሰራው መቀጠል ሰላለበት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ አርባ-ምንጭ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ነገ የአርባ ምንጭ ሰራቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ወላይታ ሶዶ ከትማ ተመልሰው የታሰሩትን የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎችን ለማስፈታት ትግሉ የሚቀጥል ሲሆን ንበረታቸውንም የማስመለሰ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ትላንትና የካቲት 25 2006 በሶዶ ከትማ ላይ ያደረጉዋቸው ሰበሰባዎች https://www.facebook.com/blueparty.ethi … =notify_me ይህንን ይመሰል ነበር፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ