የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች እየገጠሙት ነው::

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግለ ለማጎልበትና የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ ለመገምገምና ለማጠናከር እነዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ የመስክ ጉብኝት እንዲያደርጉ በሶስት ቡድን የተከፈለ ልኡካን በሃገሪቱ ማሰማራቱ ይታወቃል:: እነዚህ የልኡካን ቡድን አባላት የመስክ ጉበኝት በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ በተግባራዊ ስራ ላይ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት በሚከተለው የመስክ ጉብኝት ምደባ መሰረት በሃገሪት የተለያዩ መስመሮች የተጓዙ የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ አመራሮች …
ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሸዋ ሮቢት ጨምሮ በደሴ መስመር ላይ ያሉ የሰሜን ሸዋ የፓርቲው የዞን/የቀጠና አመራሮችን በማወያየት ጉዞውን ወደ ወልዲያ እና ደሴ ያቀና ሲሆን ……

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ የያዘ የጉዞ መስመር 2 ልዑክ ቡድን የካቲት 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከምስራቅ ጎጃም የዞን አስተባባሪዎች ጋር በደብር ማርቆስ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን 18 (አስራ ስምንት) ወረዳዎች የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ በ10 (አስሩ) ወረዳዎች ማለትም፡-
1ኛ. አነደድ 2ኛ. ደ/ማርቆስ ከተማ ወረዳ 3ኛ. ጎዛአምን 4ኛ. ማቻከል 5ኛ. ደብረ ኤሊያስ 6ኛ.ባሶ ሊበን
7ኛ. እናርጅ እናውጋ 8ኛ. ጎንቻ ሲሶእነሴ 9ኛ. እነብሴ ሳርምድርጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር/መርጦ ለማርያም 10ኛ. ሁለት እጁ እነሴ
ከላይ በተገለፁት ወረዳዎች የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ተዘርግቶ ስራዎች እየተሩ ሲሆን ወደቦታው ያቀናው የልዑክ ቡድን እነዚህን ወረዳዎች ከሚያስተባብረው የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በቀጣይ ቀናት በባህር ዳር፣ ወረታ (ደቡብ ጐንደር) እና ጐንደር በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ኢትዮጵያ ልዕካን ቡድን የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የያዘው የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶዶ ላይ ካለው መዋቅር ጋር አሰፈለጊውን ስብሰባና ግምገማ ካካሄዱ ቦሀላ ወደ ቀጣይ ከተማ ወደሆነችው አርባ ምንጭ ጉዞ ሲጀምሩ በሰዶ ፖሊሶች ተይዘው በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ ይገኛሉ::

ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ እና ምግብ እንዳይትገባላቸው የተደረጉት የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶስት አባላት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች የሆኑ ያልተማሩ ካድረዎች በበላይ ትእዛዝ በሚል ህገመንግስቱን በረገጠ መልኩ ሰላማዊ ትግልን መርጦ በመንግስት ተመዝግቦ በሚገኝ ፓርቲ እና አመራሮች ላይ የእስር እርምጃ መውሰዳቸው የዲሞክራሲ እሾዎች ማበባቸውን ያመለክታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ