በብኣዴን ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል። ሕወሓት በአማራው ክልል አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ ሊደርግ ነው።
በብኣዴን ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል።
ሕወሓት በአማራው ክልል አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ ሊደርግ ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፤ የብኣዴን ካድሬዎች ድርጅታቸውን እና አመራራቸው ላይ የሚታየውን ጉዳይ በተመለከተ የፖለቲካ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ተከትሎ ከሕወሓት አሽከር ከሆኑት ጋር በስብሰባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስብሰባው እንደተበተነ ታውቋል:: በሕወሓት እና በብኣዴን መካከል ልዩነቶች የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ተከስተው አሁንም በስፋት ቀጥለው ይገኛሉ::የተለያዩ ነባር የብኣዴን ካድረዎችን በሰብብ አስባብ የሚያንጠባጥበው ሕወሓት አሁንም አሽከሮቹን አሰማርቶ በድርጅታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲደረግ እና የሕወሓት ደባልነትና ፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያበቃ የጠየቁትን ወደ ገደል ለመግፋት አየተሯሯጠ ነው::
ባለፉት ሳምንታት በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ የተጠሩ ስብሰባዎች በሕወሓት አሽከሮች እና በለውጥ ጠያቂዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ስብሰባው ሲበተን …ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው ስብሰባ በከፊል ካድሬዎቹ ስላልመጡ ለሚመጣው ሳምንት የተላለፈ መሆኑን ታውቋል::በሕወሓት አሽከሮች እና በብኣዴን ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል::
አዲስ በወጣው እቅድ መሰረት በአማራው ክልል በድጋሚ አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ እንደሚደርግ እና በዚህ መካከል አስቸጋሪ እና አድመኞች የጸረ ሰላም እና የጸረ ሕዝብ ሃይሎችን የመደምሰስ እንዲሁም በአዲሱ የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አስፈላጊው ጥቅማጥቅሞችን ለአዳዲስ አባላት መስጠት የሚል ይገኝበታል::ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱ ችግር በፓርቲው ላይ የሚፈጥሩ ካድሬዎችን በማስወገድ በአዳዲስ ለመተካት ታቅዷል::