ሕወሓት/ኢሕኣዴግ እና የሰሞኑ ኣበይት ጉዳዮች የራሱን ጣቶች ወደ ራሱ መቀሰሩ……….

:evil:
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ልብ ብለው ከሆነ በዚህ ሳምንት ሕወሓት/እሕኣዴግ በሁለት ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ የተለይዩ ተግባራትን ከውኖ ራሱን አጋልጦ አደባባይ ላይ አምባገነንነቱን አስመንጥሮ ተሽከርክሮ አሸባሪነትን እና አሸባሪዎችን እንዳቀፈ ጉዞውን እየተንገዳገደው ነው::

ሕወሓት በዚህ ሳምንት የራሱ የውስጥ ሽኩቻ እና የኢሕኣዴግ አባል ድርጅቶች የለውጥ እንቅስቃሴ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተቱት ለመውጣት በሚይደርገው መፍጨርጨር ሌላ አዳዲስ የሽብር ድርጊቶቹን ማንገውለል ይዟል:: ያው እንደተለመደው ድሮም እጆች ሁሉ ወደ ሕወሓት ቢያመለክቱም የአሁኑ ለየት ብሎ የራሱን ጣቶች ወደ ራሱ መቀሰሩ ነው::

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ እና የሙስሊሙ ጥያቄዎች
ኢሕኣዸግ በህገመንግስቱ መሰረት በወንጀል መከሰስ አለበት::

ሓይማኖት እና ፖለቲካ እንደማይገናኙ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በሕገመንግስቱ የተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑ እየታወቀ በገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው ወንጀል በሕገመንግስቱ መሰረት ወንጀለኛው ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መሆኑ በይፋ ተረጋግቷል:: እስካሁን ድረስ መልስ ያልተገኘለት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄ በመንግስት ማነቆ እና በባለስልጣናቱ ሽብር የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ንጽሕናቸው እየታወቀ ወህኒ ቤት አስቀምጦ የራሱን ፖለቲካዊ መጅሊስ መገንብቱን በይፋ አምኗል:: በሽብር ስልት የገነባው መጅሊስ ላለው ስርኣት ትዛዥ የሚሆን እና የፖለቲካ ታማኞችን ያቀፈ መሆኑ በይፋ ማመኑ ሕወሓት ምን ያህል በሃይማኖቶች ውስጥ አብዮታዊ ዲሞክራሲን አስርጾ ለአገዛዙ በሚያመቸው መንገድ እንደቀረጸው አመነም አላመነም የታወቀውን ጉዳይ ግን በአቦይ ስብሃት በኩል ዘርግፎታል::ከቦሌ የተፈጠረው ሕገወጥ መጅሊስ በህያሉ እና አሸባሪው ሕወሓት እና መሪዎቹ ተጀምሮ እና ተስፋፍቶ እስከሽልምት ደርሶ መንግስት ሕገመንግስቱን እንደጣሰ እና በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንደገብ ሲያረጋግጥ የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ንጽሕና እንዳመነ እና ሴራው ለሽንፈት እንደዳረገው ተረጋግጥውል::

ሕወሓት ቅጥረኞቹ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

እንደፈለጉ ቢናገሩ የማይታሰሩ ሰዎች አሉ አዎ አሉ ከተቃዋሚ ፓርቲ ከጋዜጠኞች እንዲሁም ከሌላው ዘርፍ…ስም መጠቃቀስ አስፈላጊ ባይሆንም ሕወሓት ይህን ሰሞን በየፓርቲው አስርጎ ባስገባቸው ቅጥረኞቹ አማካኝነት..የኣንድነት ኣባላትን
በፓርቲው ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን እና ለገዢው ፈታኝ የሆኑ የፖለቲካ ሃሳቦችን የሚያመነጩትን ለይቶ …እንዲሁም የማይታሰሩ እንደፈለጉ የሚለፈልፉ እና የሚጽፉ ጋዜጠኞች እንደ እስክንድር ነጋ ያሉትን ጠንካሮችን አሳልፈው በ24 ሰዓት ያስያዙ ….. አሁንም ሌሎችን ከፕሬሱ እንዲወገዱ የሚሰሩ አስመሳዮች ወዘተ…..

የኣንድነት አመራሮች በሰበብ አስባብ የጻፉትን ጹሁፍ ተገን በማድረግ እና የፈጠራ ምርመራ ጀምሮ ለማዋከብ እና ለማወናበድ እንደገሃዳዊ ምክንያት ተያዘ እንጂ ዋናው የስርኣቱ አላማ ጠንካራ አመራር አባላትን በማሰር ከወዲሁ ፓርቲዉን ለማዳከም የታቀደ እና በውስጥ ቅጥረኞች እየተሰራ ያለው የብተና እና ፓርቲውን በቅጥረኞች ቁጥጥር ስር አውሎ ፓርቲውን ታማኝ ተቃዋሚ ለማድረግ የታቀዳ ሴራ ነው::

የሃይለማርያም መለሳዊ መግለጫ

ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታና ከሱዳንና ግብጽ ጋር ያለውን ድርድር አስመልክቶ ድርድሩ እንዳላለቀ ፣ የኢትዮ ሱዳን የድንበር መካለልን በተመለከተ እየተናፈሰ ያለውን መሬት ለሱዳን ተሰጥቷል የሚለውን ወሬ አስመልክቶም ይህን መሰል ወሬዎች ምርጫ ሊደርስ አካባቢ መነዛታቸው አዲስ አይደለም ያሉ ቢሆንም የድንበሩን ጉዳይ በተመለከተ ካርቱም ሄደው የፈረሙት ፊርማ ሳይደርቅ እንደለመዱት ዘባርቀዋል::

እስከ 6 ወር ድረስ ህዝቡ ይዘናጋል በሚል እደምታ መግለጫቸውን የሰጥኡት የሕወሓቱ የሃሰት ስልጡን ሓይለማርያም የቴሌኮም ችግር በማስፋፊያው ስራ ሳቢያ የተፈጠረ ነው ከ6 ወራት በኋላ ለውጥ ይታያል ሲሉ ሰው ይታዘበኛል ያልፈጠረባቸው አቶ ሃይለማርያም አይን ቀቅለው ሳያበሏቸዋልቀሩም መሰል የአዲስ አበባ የውሃ ችግርንም በተመለከተ 24 ሰዓት ውሃ የሚያገኘው የከተማዋ ክፍል 75% ብቻ እንደሆነና የተቀረውንም ለማስተካከል መንግስት ይሰራል በማለት ከባድ የሆነ ውሸት ለጥፈው ዞር ብለዋል:: የውጭ ምንዛሪ እጥረትንና የባንኮች የብድር መስጠት ብቃት መመናመንን አስመልክቶ የተነሳውን ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩየእውቀት እጥረት ይሁን ሃቅን ማድበስበስ በቂ ማብራሪያ አልሰጡበትም፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ