የፌደራል ጉዳዩች ሚኒስትር ዴኤታ ከአገር ኮበለሉ

Image

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት የነበሩትና ከሃላፊነታቸው በግምገማ ከተነሱ በኋላ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ተሹመው የነበሩት አቶ ኡሙት ኡባንግ ከአገር መኮብለላቸው ታውቋል፡፡

ከሳምንት በፊት ለሚሰሩበት የሚኒስትር መስሪያ ቤት ሳያሳውቁ ከአገር ስለመውጣታቸው የተነገረባቸው አቶ ኡሙት ኡባንግ ለቅርብ ሰዎቻቸው ወደ አገር የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው መናገራቸውን አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስፍሯል፡፡

የሚኒስትር ዲኤታውን ኩብለላ በተመለከተ በአዲስ አድማስ የተጠየቁት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ፣አቶ ኡመድ በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸው መስሪያ ቤታቸው ጉዳዮን እያጣራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡