የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ የሚገኙትን የህዝበ ሙሰሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጎበኙ ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እሁድ ጥር 4 ቀን 2006 ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እና አብረዋቸው የታሰሩትን የኢስላም ልጆች መዘየራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በዚያራውም ከኮሚቴው አባላት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የፓርቲው አመራሮች በኮሚቴው አባላት ላይ የሚታየውን ፅናት አድንቀዋል፡፡
በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ የተመራው የከፍተኛ አመራር አባላት
– የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር አቶ ተክሌ በቀለ
– የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ
– የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው
– የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ
በማረሚያ ቤቱ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ከኮሚቴው አባላት ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ ከሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የቅሊንጦ እስረኞች –
1-ሼህ መክት ሙሄ – የሼሪዓ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ
2- አቡበከር አህመድ
3- ካሚል ሸምሱ
4- አቡበከር አሊ
5- ሙባረክ አደም
6-አህመድ ሙስጠፋ
7- አብዱራዛቅ አክመል
እና ሌሎችም ሲሆኑ እነ አቡበከር ከፍተኛ የመንፈስ ጥንካሬ የሚታይባቸው ዛሬም ዛሬም ከፊታቸው ፅናት የሚነበብባቸው እንደነበር የአንድነት አመራሮች ገልፀዋል፡፡
የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠንከር ያለ ምክርና መልዕክትም አስተላልፏል፡፡ ሀገሪቷ በነፃነት ደረጃ እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ መድረሷ እንዳሳዘናቸውም ለፓርቲው አመራሮች ገልፀዋል፡፡
ኮሚቴዎቻችንን ህጋዊ ወኪሎቻችን መሆናቸውን ሳር ቅጠሉ የመሰከረው ጉዳይ ቢሆንም ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ግን በእስር ቤት እንዲማቅቁ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡
አላህ ፍትህን ያስፍንላቸው!!!
ፍትህ ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች !!!