የትግራይ ህዝብ ነጻ አልወጣምን??? ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው? እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ?
ነጻ አውጪ እስከመች???
የትግራይ ህዝብ ነጻ አልወጣምን??? ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው?
እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ?
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከአነሳሱ ሲጠነሰስ የትግራይ ህዝብን ነጻ በማውጣት ሲሻው በመገንጠል ሲሻው ታላቋን ትግራይ በመመስረት ….በሚሉ የመከኑ ይሁኑ ገና ያልተሳኩ አሊያም (በፕሮሰስ ላይ ባሉ ?)ባልታወቁ መርሃግብሮች ላይ ተነድፎ ወደ ጫካ መግባቱ እውን ቢሆንም ያላሰለሱ ድሎች መገኘት የጀመሩት ግን በ1980ዎቹ የሃገራዊ ፋይዳው ታይቶ ከተፈጠሩት ሁሉን አቀፍ የጦር አውድማዎች በኋላ ነው::…ሕወሓቶች ኢሕዴንን እና ኦሕዴድን አጣምረው ኢሕኣዴግ በሚል ተሰይመው የነበሩት የዛኔዎቹ ታጋዮች ለዲሞክራሲያዊ ምስረታ እና ለህዝባዊ እኩልነት የታገሉ መሆኑ እሙን ቢሆንም የተነሱበት አላማ የተሰዉለት ይህ ነጥብ ግን ከአፈር ጋር ደባልቀውታል:: የሰምዓታቱንም ፍሬ እዛው በረሃ ጥለውት መተዋል::
የዳግማይ ወያኔ አነሳስ የትግራይን ህዝን ነጻ ለማውጣት ነው እስካለ ድረስ እና ራሱን የትግራይ ህዝቦች ነጻ አውጪ ብሎ ከሰየመ በኋላ ደርግን መፋለሙን ተከትሎ ከደርግ ጭቆና የትግራይን ህዝን ነጻ እንዳወጣው እየነገረን ነው::አሁንሳ ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው? እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ? ወይንስ ነገሩ ከወዲሁ ነው የቀድሞዎቹ ጨቋኝ መደቦች እነእንትና ካልወደሙ የህ ሕወሓት የሚለው ስሙን አይቀይርም??/
ሕውሓት የትግራይን ህዝብ ነጻ ወተሃል ካለው 22 አመት አልፎታል:: የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ገዢዎች ግን አሁንም ይህንን ስም ይዘው ቀጥለዋል::ለምን ግን …? የትግራይ ህዝብ ነጻነቱ የሚረጋገጠው ሕወሃትም ስሙን ቀይሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የሚባልበት ቀን ይናፍቃል:: ኢህዴን እንኳን መዐሕድን ተከትሎ /ቀንቶ ብኣዴን ተብሏል…ሕወሓት ግን እስከመቼ ድብቅ አላማ ይዞ እንደሚጓዝ አልረዳ ብሎናል:: ወይስ ይህን ስም የሚጠቀመው አንድ የትግራይን ነጻነት እንደኤርትራ በሪፍረንደም እስኪያስረግጥ ነው ወይንስ እነእንትና…እንስም አይጠሬ የድሮዎቹ የጨቋኝ መደቦች የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን ዘራቸው ከምድረ እትዮጵያ ተጠራርጎ እስኪጠፋ…???? የህገመንግስቱ አንቀጽ 39 ባለበት የሚቆየው ምን እስኪመሰረት ድረስ ነው? የመጀመሪያው የሆነው ኢትዮጵያዊነትን ከአያት ቅድመ አያቱ የወረሰው የትግራይ ህዝብን በአምባገነኖች ጭቆና ስር ለማስቀጠል ይሆን??/ስላልገባን ይነገረን::