የነጻነት እና የአፓርታይድ ነገር ሲነሳ ወያኔ ምነው ሆዱን ያመዋል?

የታላቁን የነጻነት ታግይ መሞት ተከትሎ ከወያኔ ጎረምሶች የሚወረወሩ ቃላቶች የፖለቲካ ብስለትን ያላገናዘቡ እና የስልጣን ጥመኝነትን የሚያሳብቁ የጭፍን ድጋፍ ሩጫዎች ሲሆኑ ማንዴላን በተመለከት ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን የሚወረወሩ የነጻነት ስሞች እና የአፓርታይድ ቃላቶች የውስጥ ህመም ሆኖባቸው ሟች አምባገነናቸውን እያነሱ መቀባጠር ጀምረዋል::

የማንዴላ ሞት አለም ያለቀሰበት የአሜሪካ ባንድራ ለ3 ቀን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ (President Barack Obama ordered American flags to be lowered immediately to half-staff until Monday in tribute to Mandela, a rare honor for a foreign leader.)የተወሰነበት ነጭ ከጥቁር ሳይል ክብሩን የገለጸበት መሆኑን በወያኔ ጎረምሶች ለምን መካድ እንደተፈለገ አይገባኝም ? የተቃዋሚ ሃይሎች ለማንዴላ ሞት ሃዘናቸውን ስለገለጹ? አሊያስ የአለም ህዝብ አትኩሮቱ ሁሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስለሆነ? ወይንሳ ለመለስ ሞት የህን ያህል …አለመደረጉ ?

ደቡብ አፍሪካ ላይ ሌጋሲ የሚባል ነገር ወላ የፖለቲካ ህዳሴ አሊያም የሚዲያ ፍጆታ ወሬ ምንምን አይሰራም:: የማንዴላ ጣኦትነት አይሰበክም :: የማንዴላ ሌጋሲ አይሰበክም :: የምንሰማው በጽናት የሃገራቸውን ነጻነት ያረጋገጥኡ በአለም አቀፍ ደረጃ የነጻነት ቀንዲል የሰላም እና የአንድነት አባት መሆናቸውን እና ፈለጋቸውን እንድንከተል እንጂ ትራንስፎርሜሽናቸውን እያጨበጨብን እንድንቀበል አይደለም::

ወያኔ የሚሰራውን ግፍና ሰቆቃ ስለሚያውቀው የነጻነት የዲሞክራሲ ጥያቄ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር ራስ ምታት ይሆንበታል:: በአለም አቀፍ ደረጃ ለዚህ የታገሉ ሰዎች ስማቸው ሲጠራ ያመዋል:; አብሶ ተቃዋሚዎች ከተናገሩ ያቃጥለዋል:: አጸ ምንሊክ … ቀኃሥ … ማንዴላ… ምናምን እየተባላ ሲተራ ያሳክከዋል ..ያራውጠዋል:….. የአገዛዝ ስልቱ በኒዎ አፓርታይድ ላይ ስለተመሰረተ የደቡብ አፍሪካው የጸረ አፓርታይድ ትግል ሲነሳ የስልጣን ማስረዘሚያው ዘዴ የተነቃበት ስለሚመስለው ይጨፍራል ለማዘናጋት ይራወጣል:: ኢትዮጵያውያን ስለእንደዚህ አይነት ነገር መስማት የለባቸውም:: አርፈው መገዛት አለባቸው ይህ ከተነሳ ወያኔ በሽታው አብሮ ይነሳል ይፈራል:ስራውን ስለሚያውቅ::

የዛሬው የወያኔ ጎረምሶች ጭፈራ በከፊል የህን የተመረኮዘ ነው::በአለም በአፍሪካ በሃገር ቤት አንድ ነገር በመጣ ሰአት ሁሉ ወያኔ የሚለቃቸውን የፖለቲካ ፍጆታ ነጠላ ዜማዎች ለማቆም መጣር እንዳለበት ልንመክረው እንፈልጋለን::