ከሰሞኑ ሴራዎች በስተጀርባ

ሴራ የአምባገነኖች ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡

ህዝብን ለማወናበድመ ትኩረት ለማስቀየር፣ ለመከፋፈል በአጠቃላይ ዋነኛ መግዢያ መሳሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ምንም ይሁን ምን ሴራ ካልሰሩ ስልጣን ላይ የሚኖሩ አይመስላቸውም፡፡ አምባገነኖች የሴራ ሱስ ጠጠቂዎች ናቸው፡፡ ከወራት በፊት ነው፡፡ ኢቲቪ ስለ ስደት ተደጋጋሚ ዘገባዎችን፣ ዶክመንተሪዎችን ማሳየት ተያይዞት ነበር፡፡ ከዛም የሳውዲ አረቢያ መንግስት ስደተኞች እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በህጋዊ መንገድ የሚሄዱትንም ጭምር አገደ፡፡

ለባለስልጣናት እንደ ምትታለብ ላም የሚቆጠሩት ኤጀንሲዎችም ሳይቀር ስራ እንዲያቆሙ ተነገራቸው፡፡ በጊዜያውይነትም ታገደ፡፡ ብቻ እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት አንድ ያሳሰበው ነገር እንዳለ ማየት ይቻላል፡፡ ለስደተኞች አዝኖ እንዳልሆነ በስተመጨረሻ የደረሰውን ሰቆቃና ሰቆቃው ሲደርስ የወሰደው የረባ እርምጃ አለመኖሩ ያስረግጣል፡፡ እኔ በበኩሉ አንድ ሴራ ይታየኛል፡፡ በዓረቡ አለም የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ልክ በአሜሪካና አውሮፓ እንደሚኖረው ዲያስፖራ የተቃውሞ ምንጭ መሆን ጀምረዋል፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚንቀሳቀሱት በአረቡ አለም የሚገኙት ወገኖቻችን ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ የአይበገሬው ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› አባላት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የዚህን ቡድን ድምጽ ሲሰማ ይበርክካል፡፡ ጭንቅ ይለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ‹‹አማካሪ›› ነን ባዮች የኢትዮጵያን ስደተኞች የድምጻችን ይሰማን ጨምሮ የተቃውሞ ጎራውን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን አምነዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ግን መንግስት የሚወቅሰውን አክራሪነት መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው አስበዋል፡፡ ያው ‹‹አማካሪ›› ነን ባዮቹ የሚናገሩት መንግስት ሊሰማ የሚፈልገውን ነውና የሚፈሩትን ለጥፈውባቸዋል፡፡ ሳውዲዎች ደግሞ ስራ አጣን ብለው እያማረሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ እና ከመንግስቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ስደተኞቹን እንደ ጠላት ያዩዋቸዋል፡፡ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውን ከስደታቸው አልቆሙም ነበር፡፡ እናም አንዳች ነገር መደገስ ነበረባቸው፡፡ ስደተኞቹ በተለይም የመንግስት አማካሪ ነን ባዮች ‹‹አክራሪዎች›› ይፈለፈሉባታል ከሚሏት ሳውዲ ‹‹አይቀጡ ቅጣት›› ተቀጥተው እንዲመሰሉ ማድረግ፡፡ ሌሎች እንዳይሄዱ ‹‹ትምህርት›› መስጠት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለተመላሾች በሚያደርገው ‹‹ድጋፍም›› የሆነች ጥቅም እንደሚያገኝበት ገምቷል፡፡ ታዲያ ኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ለምን ደረሰ? በሳውዲ መንግስት ላይ ምንም አይነት ጫል አልተደረገም? መንግስት ለምን ትክክለኛ እርምጃ ለመውሰድ ተደናረ? ለምንስ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉትን ደበደበ? የሀይለማሪያም ደሳለኝ ዝምታስ? ሌላ ሴራ ከትናንትና በፊት መቀሌ ከአንዴም ሶስቴ መንደዷን ሰማን፡፡ ከዛም መርካቶ፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ለኢህአዴግ መቀመጫ የነሳው ሙስሊም የሚበዛበት አካባቢ ነው፡፡ መርካቶ የእንቅስቃሴው መሰረት ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ቢደርስ ትኩረት ሊስብ ይችላል በሚል መቀሌን ቀድመው ያነደዷት ይመስለኛል፡፡ ደግሞ በሁለቱም ከተማ የወደሙት ሱቆች ናቸው፡፡ ለምን? የንግዱን ማህበረሰብ ለማሸበር? ትኩረትን ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባና መቀሌ ለማስቀየስ? ‹‹አክራዎችን ገቢ ለማሳጣት››? ማን ያውቃል ‹‹አማካሪዎቹ›› የማይዘይዱት አይኖርም፡፡ ሁሉም ድራማ ነው፡፡

እሳቱ በቁጥጥር ስራ ሳይውል በቁጥጥር ስር ዋለ ማለቱን ለምን አስፈለገ? በቅርቡ ኢህአዴግ ከአማካሪዎቹ ‹‹49 በመቶ በላይ የኑሮ ውድነት ይከሰታል፡፡›› ተብሎ እንደተነገረው ተሰምቷል፡፡ በክርክር ላይ ናቸውም ተብሏል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ምክንያት ከተባሉት መካከል ደግሞ ‹‹ከ39 አይበልጡም!›› የሚባሉት የመርካቶ ነጋዴዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ነጋዴዎች ‹‹ድምጻችን ይሰማ››፣ በኑሮ ውድነትም ይከሷቸዋል፡፡ ብቻ ሴራው ይታየኛል፡፡ አምባገነኖች ከገቡበት ማጥ ለመውጣት ሴራን ዋናው ስልታቸው ያደርጋሉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ውጤትና ምክንያቱን ሳይመዝኑ የተለከፉበትን ሴራ ይሸርባሉ፡፡ በተራ ግለሰባዊ ጠብ፣ በጥላቻ አገርና ህዝብ ያቃጥላሉ፡፡ ይወራሉ፡፡ ጦርነት ያስጀምራሉ፡፡ በሽታ እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ፡፡ ዞረው የመፍትሄው አካል መስለው ይታያሉ፡፡ ይለምኑበታል፡፡ የዜጎቻችን ሰቆቃና የከተሞቻችን ቃጠሎ ሴራ ሴራ ይሸተኛል፡፡ ይህ መንግስት እኮ ሀውዜንን ማስጨፍጨፉን የቀድሞ አባላቱ ተናግረዋል፡፡ የአበበች ደራራን አባት መግደሉን ካድሬዎቹ መስክረዋል፡፡ የደሴውን ሸክ መግደሉን ህዝብ እየተናገረ ነው፡፡ አንድ ቀን የሚወጣ ይሆናል፡፡