ድምጻችንን ከማሰማት አንቆጠብ..የኢትዮጵያ መንግስት ማላገጡን በሳዑዲም ዜጋችን መሞቱ ቀጥሏል..
ድምጻችንን ከማሰማት አንቆጠብ..የኢትዮጵያ መንግስት ማላገጡን በሳዑዲም ዜጋችን መሞቱ ቀጥሏል..
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ሪያድ ውስጥ ወገኖቻችን ላይ ዛሬም ጥቃት ተፈጸመ፡፡ ብጥብጥ ተፈጥሯል እባክህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውልልኝ ብሎ ቁጥር አስቀምጦልኝ አገኘሁ፡፡ 9665533…አደረኩና ደወልኩ፡፡ ከወዲያ ማዶ ምላሽ ስጠብቅ ኮለል ያለ የመደፈር ጥቃት የአትንኩኝ ባይነት ግርማ ሞገስ ባለው ድምጽ ‹‹ሀሎ!›› ተባልኩ፡፡ ሰላምታዬን አደረስኩና ብጥብጡ ምንድን ነው አልኩት፡፡ ‹‹..ይሄውልህ ግሩሜ በሪያድ መንፉሃ አውራ መንገዶች ሃገራችን ውሰዱን ብለን እቃችንን ሸጠን ወጥተናል፡፡ አምባሳደሩ መጣና ምንም ችግር የለም ወደ ሀገር ትገባላችሁ ብሎ ሄደ፡፡ ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ ብጥብት ተነሳ….(ዛሬ የሚለው ትላንት ማታ ስላውራሁት ነው)
(እኔ እሱን ላቋርጥና የምለው ስላለኝ ቅንፌን ከፍቻለሁ፡፡ አምባሳደሩ በሉ ተብለው የታዘዙትን ነው ያሉት፡፡ ያ-ሳይሆን የሚያሳዝነው ቤታቸውን ጥለው ወጥተው አደባባይ መሆናቸውን እያዩ አላግጤ ንግግራቸውን ተናገው እና በአፍ ደልለው መሄዳቸውን ሌላ ምንጮቼ ገልጸውልኛል፡፡ ዜጋዬን..ያለው መንግስትም 25 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር መመለሱን በዜና እወጃው አሰውቋል፡፡ የተመለሱት ሰዎችን ምንነት በዜናው ላይ ከተደረገላቸው ቃለ-ምልልስ ማወቅ ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች ዘውትር የሚያንቆረቁሩት ስልቹ ቃላትን ሲደግሙት ለሰማ ‹‹..አሀ! የእንትን ልማት ማህበር አባል…›› ብሎ መጥራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ጥርጣሬዬን ይዤ ለአንዱ እንዴት ነው ለመግባት ያለው ሂደት አልኩት፡፡ ‹‹.1000 ሪያል ካለህ በአፋጣኝ ትጨርሳለህ….›› በስመአብ የደነገጥኩትን አትጠይቁኝ፡፡…እኔ በአረቡ አለም ያሉት ኤምባሲዎች ኮሙኒቲ ካልተመዘገብክ የአማራ ልማት ማህበር፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣የጉራጌ..ምናምን አባል ካሆናችሁ እያሉ አገልግሎት ስለማጓተታቸው ስጠይቀው ይባስ ለፈጣን አገልግሎት 1000 ሪያል ጉቦ መባሉ እንዴት አያስደነግጠኝ? አሁን ለደወልኩለት እና እያናገርኩት ላለው ልጅም ይሄን ጥያቄ አቀረብኩለት…ወደ ዘገባዬ ተመለስኩ፡፡)
ወደ ሀገራችን መልሱን የሚለው ጥያቄያችንን ለማደናቀፍ ፖሊስ ሸባቦቹን ይዞ መጣ፡፡ (ሸባብ ማለት ወጣት ነው፡፡ ፖሊስ እነዚህን የመንደር ጎረምሶች ይዞ በመዞር ነው ዜጋዎቻችን ላይ ጥቃት የሚፈጽመው) ‹‹ለምንድነው እንደዚህ የምትሆኑት ሂዱ ብላችኋል መሄድ እንፈልጋለን ብለን ነው ቤት ንብረታችንን ጥለን የመጣነው ብለን ለማረጋጋት ሞከርን፡፡ በፊት ሲመጡ አሰር (የዘጠን ሰዓት ስግደት) እየሰገድን ነበር፡፡ በተፈጠረው ግርግር ሲያሰግደን የነበረውን ልጅ በጩቤ ወጉት፡፡ ከዛ ከፍተኛ ግርግር ነበር፡፡ ወደ ታፋው አካባቢ ነው የወጉት፡፡ እንግዲህ ኤምባሲው ምንድን ነው ስራው…(ወዳጄ የኤንባሲው ስራ እናንተን ማስደብደብ እና ከሳዑዲ የሚፈልጉትን ማግኘት) እንዴት ነው በዚህ ጭንቅ ሰዓት ኤምባሲው የሚያስከፍላችሁ ነገር አለ እንዴ? አልኩና ጥያቄ በስልክ ወረወርኩ፡፡ ቀበል አለና አይ! ጉዳዩን ቶሎ እንዲጨርሱልህ ላለመጉላላት ከፈለክ 1000 ሪያል የይጠይቁሀል….(ጉቦ መሆኑ ነው ወገኖቼ በዚህ የጭንቅ ሰዓት እነዚህ የኤምባሲ ሰራተኞች ጉቦ ይበላሉ…..የወገናቸውን ደም ይጠጣሉ፡፡ ኧረ!!!!…እባካችሁ እንተዛዘን….) ሌላው አሁንም የገዚው ፓርቲ አሸርጋጆች በድርጅታዊ አወቃቀር ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊን እንደ ዜጋ በማየት ማስተናገድ እንጂ በዚህ ሰዓት አባል የሆና ያልሆነ እያላችሁ እና ከዜጋ ህይወት ገንዘብ አስበልጣችሁ ኪሳችሁን ማደለብ ስታስቡ አሁንም ወገኖቻቻንን ለእልቂት አትዳርጉ፡፡
በዙሪያው የምንገኝ የመንፉሃን ግጭት ተከትሎ በተሰጠው ወደ ሃገር የመግባት እድል ለመጠቀም በቡዙ ሺህ የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊ መጠለያዎችን እያጨናነቀ ነው። በመካ ያለው ከባድ ሁኔታ ቢሆንም ያለው የባሰ ያስገረመው በሁለት ኢትዮጵዊያን መካከል በተፈጠረ ግጭት አንደኛው አንዱን ደጋግሞ በጩቤ በመውጋቱ አንደኛው ኢትዮጵያው ለህልፈተ ህይወት በቅቷል፡፡ ይህ ወገን ወገኑን የሚጎዳበት ሂደት በእንደዚህ አይነት አጣብቂኝ የስቃይ ህይወት ውስጥ ሆኖም መቀጠሉ ያሳዝናል፡፡
አሁንም በሽዎች የሚቆጠሩ ወደ መጠለያ ለመግባት እየጎረፉ ነው ። በመጠለያው ትናነት አንዲት የ9 ወር እርጉዝ ሞታ ተቀብራለች ። በመጠለያው የምግብና የመጥ እጠረቱ ደግሞ ኢትዮጰያውያኑነ አጥር ሰብረው እንዲወጡ እያስገደደ ነው ተብሏል። በሳዑዲ ያለው ሁኔታ መንግስት ቀዝቅዟል በማለት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በኩል ቢናገርም ቢገልጽም፡፡ሁኔታው የከፋ እና ፖሊስ አሁንም ወጣቶችን ይዞ በየቦታው እየዞረ ማስደብደቡን እንደቀጠለ መሆኑን ሳዑዲያ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ይናገራሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ መረጃ እየሰጡ ያሉት የመንግስት ተቋማት ዛሬም ይህንኑ እየደገሙት መሆኑ አሳዛኝ ኢ-ሰብአዊነት እየፈጽሙ መሆኑን ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡
ከከተማው አርቀው ያስቀመጧቸው ካምፐ ውስጥ የምግብ እና ውሀ እጥረት መኖሩን አንድ መረጃ ሲያቀብለኝ የከረመ ወዳጄ አድርሶኛል፡፡ ሴቶች፣ ህጸናት፣.የስኳር በሽተኞች፣ አሉ፡፡ ካምፕ ውስጥ አስገብተው ከቀን አንዴ ብቻ ነበር እህል የሚሰጠን፡፡ አሁን ድንገት ሁለት ነው ማለት ከተቻለ ሁልቴ አንዴ የምትበላውን የሚያህል ያበሉሀል፡፡ የመጠለያው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ነግሮኛል፡፡ በተጨማሪም በእስር እና ከእስር ወደ እስር ቤት መቀየር ላይ አስካሁን ብቻ 5 ሰዎች መሞታቸውን ይሄው የአይን እማኝ የሆነው የመረጃ ምንጬ ገልጾልኛል፡፡ በግሩም ተ/ሀይማኖት