በቁጫ ወረዳ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች እየተባረሩ ነው

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል።

እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ታስረዋል።

ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ችግር በ48 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሽፋን 45 በመቶ መቀነሱም ታውቋል።

ተቃውሞውን አስተባብሮአል የተባሉት መአቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*